❤ክርስትና በማሕበራዊ ሕይወት❤
ቆላ:3 23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ ቆጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
❤ ለእግዚአብሔር ብሎ መስራትና ለሰው ብሎ መስራት ልዩነቱ ምንድን ነው?
1, ከልብ /ከእሳቤ አንጻር/ Difference in intention.
1.1 ለእግዚአብሔር ብሎ የሚሠራ
🥰 በረከትን አስበን ስለኾነ በደስታ ነው
🥰የሚሠራውን ኹሉ በንጹሕ ልብ ያከናውናል ይሠራል
1, 2 ለሰው ብሎ የሚሠራ
🤨 በስም አደረገ ለማለት እንዲወራለት በመፈለግ
🤨 ለመሸለም ለመኮፈስ
🤨 ከሌላው ጋር ለመፎካከር
2, የሚገኘው ዋጋ
2.1 🥰 ለእግዚአብሔር ብሎ የሚሠራ በስውር የሚሰጥ አባትህ በግልጽ ይከፈለዋል ለእግዚአብሔር ብሎ የሠራ
2.2 ለሰው ብሎ የሚሰራ (ውዳሴ ከንቱ )
🤨 ምድራዊ ነው ዋጋው
በጌታ ፊት ዋጋ የላቸውም በምድር ዋጋቸውን ተቀብለዋልና (ማቲ: 6,2)
ዋጋቸው ክፍያ ሊሆን ይችላል ወይም ሙገሳ ወይም ውዳሴ ከንቱ
3. ከአቋም ዘላቂነት አንጻር
ከእግዚአብሔር ጋር የኾነ
3.1 🥰 ብቻውን ቢኾንም በሰው መኻል ቢኾንም ይሰራዋል።
3.2 ሰው የሚሠራ ቋሚ ማንነት የለውም ሰው ባለበትና በሌለበት በብዙ ሰውና በጥቂት ሰው መኻል...
🥰 በክርስትና በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ስንኖር ብቻ የምናደርገው ሕይወት ሳይኾን በቤታችሁ በሥራ ቦታችሁ በማኅበራዊ ግንኙነታችን ፤
🥰በማኅበራዊ ሕይወታችን ያለንን ግንኙነት የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ መሆን አለበት ለምሳሌ ፦
🥰 ለልጆቻችን የምናደርገውም የተለያዩ ድግሶች
🥰 ግብዣ
🥰 ልደት ሰርግ የተለያዩ ....
እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከእንቅብ በታች..... ማቲ 5:14-16
🥰 በጸሎት ጀምሮ በስካር መጨረስ በመዝሙር ጀምሮ በዘፈን መጨረስ አግባብ አይደለም።