#ሕይወትን_መጠበቅ (2) በዔድን ውስጥ አዳም እንደተባለው በዚኽ ዓለምም እንዲኹ ነው ሕይወትን ማልማት፥ መንከባከብ እና መጠበቅ ያስፈልጋል። በዔድን የሚሰራው ተመሳሳይ Principle ነው አኹንም የምሰራው። ጌታን ስንቀበል ሁላችንም ሕይወት ተቀብለናል ግን ማልማት፥ መንከባከብ እና መጠበቅ ይኖርብናል ካልኾነ ከአሕዛብ አንሻልም። አዎን በክርስቶስ ነን ከገሃነም አምልጠን የዘላለምን ሕይወት አግኝተናል ቢኾንም ማልማት፥ መንከባከብ እና መጠበቅ ይኖርብናል። ዔድን ማለት በእግዚአብሔር ለእኔና ለእናንተ ጥቅም በክርስቶስ ኢየሱስ የቀረበልን ሕይወት ነው። ዔድን Geogeraphical Location ማለት አይደለም ዔድን ከእግዚአብሔር የተቀበልነው መንፈሳዊ ስፍራችን ነው። እግዚአብሔር አዳምን በዔድን እንዳኖረው እያንዳንዱ ሰው እጁን አንሥቶ ጌታን ሲቀበል ወደ ዔድን ተመልሶአል። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ለሰው ልጆች አድስ Plan አይደለም ያወጣው። መጽሐፍ ክርስቶስ ከእርግማን ዋጀን ይላል። የሚዋጀው መጀመሪያ የነበረ ነገር ነው። ያልነበረ ነገር አይዋጅም። ያልነበረ ነገር መጣ፥ ተገኘ፥ ተፈጠረ ነው እሚባለው። ስለዚኽ የዋጀው የመጀመሪያው አዳም የጣለውን ሕይወት ነው። ያንን ሕይወት ጌታ ባይመልስልን ኖሮ ዲያብሎስን አልቀጣውም ማለት ነበር። ሰይጣን የተቀጣው ከመጀመሪያው አዳም የነጠቀውን ሕይወትና ስልጣን ክርስቶስ ወደ ሲዖል ወርዶ አለቅነቱንና ስልጣኑን ገፎ ስወስድበት ነው። ስለዚኽ መጽሐፍ “አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው” (ቆላስይስ 2፥15) ይላል። #ዔድን_ለእኛ_እሚናድግበትና_የምናብብበት_መንፈሳዊ ስፍራችን ነው። ስለዚኽ በክርስቶስ ወደ ሐይማኖተኝነት ሳይኾን የገባነው ወደ ሕይወት ነው። ይኼ የቃል ብርሃን ወደ ሕይወታችን እየገባ እየገባ ሲመጣ ሕይወታችን ሙሉበሙሉ ይቀየራል። ከእንግዲኽ በኋላ የትም ሲትኼዱ ከራሳችሁ ጋር ዔድንን ይዛችሁ ነው እሚትኼዱት። ይኼ መገለጥ ሲገባችሁ ሕይወት በእናንተ ይበቅላል። #አንዳንድ ሰው ታዲያ አኹን ዔድን ከገባሁ ገንዘብ ለምን ያጥረኛል? ለምን በእጥረት ውስጥ እገኛለሁ ልል ይችላል። መልሱ አልማው፥ ተንከባክበው፥ ጠብቀው ነው። ያኔ የተካፈላችሁት ሕይወት ያስደንቃችኋል። አያችሁ በኪሳችሁ ገንዘብ አላችሁ ማለት Exchange ካላረጋችሁበት አይጠቅማችሁም። የገንዘብ አቅም ያለው በExchange ላይ እንጂ ኖቱ ላይ አይደለም። በተመሳሳይ መንገድ በእኛ ያለው ሕይወት ፍሬ እስካላፈራ ድረስ ጥቅም የለውም (Beneficial አይደለም)። ስለዚኽ የተቀበላችሁትን መለኮታዊ ሕይወት፥ መለኮታዊ ብልጽግና፥ መለኮታዊ ኅይል፥ መለኮታዊ ጥበቃ፥ መለኮታዊ ፈውስ፥ መለኮታዊ እረፍትና መለኮታዊ ደስታ መግለጥ ስትጀምሩ ለእናንተ ጥቅም መሥራት ይጀምራል። አንዳንድ ሰዎች አሉኮ ገንዘባቸውን Exchange ላለማድረግ በካዝና ውስጥ ደብቀው ለረጅም ጊዜ ቁጭ እሚያረጉ እነዛ ሰዎች የሞቱ ናቸው። ክርስቲናችንም ተመሳሳይ ነው ። ዔድን በውስጣችን ነው ያለው ስለዚኽ እናተርፍበት፥ የሚያስፈልገንን እንያዝበት። የእግዚአብሔር የራሱ ሕይወት በእኛ ውስጥ አለ። አዳም ወደ ዔድን እንደገባ እኛም ወደ እግዚአብሔር ሕይወት ተጨምረናል። ለዚኽ ነው መጽሐፍ “እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል ይህም የድነታችሁን ወንጌል በሰማችሁ ጊዜ ወደ ክርስቶስ ተጨምራችኋል፤ አምናችሁም፣ በእርሱ በመሆን ተስፋ ሆኖ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ታትማችኋል” (ኤፌሶን 1:13 አ.መ.ት) የሚለን። #ዔድን ማለት ለእኔና ለእናንተ ሕይወታችን የሚያፈራበትና የሚባዛበት ስፍራችን ነው። ለማብዛትና ለማፍራት የተሾምንበት ቦታ ነው። መጽሐፍ ፍሬያማ ኹኑ ያለን ለዚኽ ነው። ፍሬያማ እንድንኾን ነው ዔድን እንደገና በክርስቶስ የተሰጠን። ዔድን ለሕይወታችን መለኮታዊ አቅርቦት የምደረግበት አዳራሻችን ነው። መለኮታዊ አቅርቦትን Exprience እሚናደርግበት ስፍራ በክርስቶስ እንደገና ገብተናል። እንግዲኽ አኹን በዔድን ውስጥ ነው ያለነው። ይቀላቀላሉንhttps://t.me/TheimageofChrist1 ለሌሎች 👉👉shareማድረግን እና #Add👈👈 ማድረግን አትርሱ
ሕይወትን_መጠበቅ (2) በዔድን ውስጥ አዳም እንደተባለው በዚኽ ዓለምም እንዲኹ ነው ሕይወትን ማልማት፥… — Sonship in Christ — TG.ME
August 14, 2025 333 1