እሁድ በGrace life community church በመጋቢ አማረ የተካፈልነው ቃል ። ጊዜን በተመለከተ… — Sonship in Christ — TG.ME

እሁድ  በGrace life community church በመጋቢ አማረ የተካፈልነው ቃል ። ጊዜን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ሦስት የግሪክ ቃሎችን ይጠቀማል። 1. አዮንስ - ያለፈውን የአሁኑን እና የወደፊቱን ዘመን አመልካች ሲሆን "[4] እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ፣ ከዚህ ክፉ ዓለም ያድነን ዘንድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን ሰጠ፤" (ገላትያ 1:4 NASV) 2. ክሮኖስ - ጊዜን አመልካች 3. ካይሮስ - የእግዚአብሔር ጊዜ "[24]  እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።" (መዝሙር 118:24 NASV) የእግዚአብሔር ሀሳብእና እቅድ የተፈጸመበት ጊዜ ነው። የነገር ውበትና ድምቀት ያለው በጊዜ ውስጥ ነው። "[11] ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።" (መክብብ 3:11 NASV) የተገለጠ ሕይወት የሚገናኘው ከጊዜ እና ከመንቃት ጋር ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር እውቀት ስንነቃ ሕይወት ይበዛልናል። "[25] በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር። [26] ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤ [27] እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ [28] ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤ [29] “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣ አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤ [30] ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣ [31] ማዳንህን አይተዋልና። [32] ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።" (ሉቃስ 2:25-32 NASV) "[14] ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።" (ኤፌሶን 5:14 NASV) ያልነቃ ሠው ነው ዘመንን የሚያስበላው። "15እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። 16 ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። 17 ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ።" ኤፌሶን 5:15-17 "32 ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።" 1ዜና መዋዕል 12:32 ይኼን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተመልከቱት - ዘፍ 41:16-57 ኢየሱስ የተገለጠ ሕይወት ስለነበረው ጊዜውን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። "2 የአይሁድ የዳስ በዓል በተቃረበ ጊዜ ግን፣ [3] የኢየሱስ ወንድሞች እንዲህ አሉት፤ “ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ የምታደርገውን ታምራት እንዲያዩ፣ ከዚህ ወደ ይሁዳ ሂድ፤ [4] ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።” [5] የገዛ ወንድሞቹ እንኳ አላመኑበትም ነበር። [6] ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ምቹ ነው። [7] ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን፣ አድራጎቱ ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት ይጠላኛል። [8] እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ስላልደረሰ ወደ በዓሉ አልሄድም።” [9] ይህን ብሏቸው በገሊላ ቈየ።" (ዮሐንስ 7:2-9 NASV) የተወደደ ሰዓት ትላንት ወይም ነገ ሳይሆን አሁን ነው። "[2] እርሱ፣ “በትክክለኛው ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።" (2 ቆሮንቶስ 6:2 NASV) ካይሮስ ካመለጣችሁ መልሳችሁ አታገኙትም። "[4] ቀን ሳለ፣ የላከኝን ሥራ መሥራት አለብን፤ ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል፤" (ዮሐንስ 9:4 NASV)

August 11, 2025 353 3