🍃 -ዱንያ-
እጅግ በጣም አስተማሪ ስለሆነ አንብበን ስንጨርስ ለሌሎችም እናካፍል
በዱኑ ውበት ተማርኮ ዛፍ ቅጠሉን እያየ ሳለ ነበር ከኃላው አንዳች የሚንኮሻኮሽ ድምፅ የሰማው...ምንነቱን ለማረጋገጥ ዞረ...ከኃላው የነበረው አንበሳ ነበር አይኑን ማመን አቃተው ደነገጠ እግሬ አውጭኝ ብሎም መሮጥ ጀመረ...አንበሳውም ተከተለው ጥቂት ከሮጠ በኃላ የውሃ ጉድጓድ አየ ሌላ ምንም አማራጭ ስላልነበረው ዘሎ የውሃ ማውጫው ገመድ ላይ ተንጠለጠለ ...አንበሳውም እያጎራ ይጠብቀው ጀመር...ድንገት ወደ ታች ሲመለከት የውሃ ጉድጓዱ የቆየ ነበርና የእባቦች መጠራቀሚያ ሆንዋል ...የሰውየው የልብ ምት ጨመረ ከላይም ከታችም ሁለት አስፈሪ ነገሮች ተጋርጠውበታል ...የውስጡን ፍረሀት እያስታመመ ወደ ላይ ቀጥ ሲል ሁለት ነጭና ጥቁር አይጦች ገመድ የታሰረበት እንጨት ላይ ሆነው ገመዱን ሲቆረጥውት አስተዋለ "ኦ ጌታየ ዛሬ የመጣብኝ መከራ"ብሎ አይጦቹን ለማባረር ገመዱን በማወዛወዝ ማንቀሳቀስ ጀመረ ...ወደ ቀኝ ወደ ግራ ራሱን ሲያንቀሳቅስ ከአንዱ የጉድጓዱ ጎን የሆነ ወፈር ያለ ፈሳሽ ነገር ነካው በደንብ ቀረብ ብሎ ሲመለከት በጉድጓዱ ግድግዳ ድንጋይ ክፍተት ውሰጥ ንቦች ማር ጥለው ነበር ...ሰውየው የነበረበት መከራ ከላይና ከታች የሚጠብቁትን ነገሮች ረስቶ ማሩን መላስ ተያያዘው ማሩ በጣም ጣፋጭ ነበርና ያለበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ረሳው...ድንገት ከእንቅልፉ ባቶ ነቃ፦ በጣም አስፈሪና የሚረብሽ ህልም ነበር ሲያይ የነበረው። ህልሙን ወደ ሚፈታለት ሰው ለመሄድ ወሰነ ወደ አንድ ህልም ፈች አዋቂ ሰው ሄደና ህልሙን አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገረው ሸህየውም ሳቀና የህልሙ ፍቺ አልገባህም ሲል በመገረም ጠየቀው ሰውየውም መልሱን እንዲህ ብሎ መለሰለት
-ከኃላህ ሲያባርህ የነበረው "መሊከል ሞት"ነው
-እባቦች ያሉበት ጉድጓድ ደግሞ ቀብርህ ነው
-የተንጠለጠልክበት ገመድ ደግሞ እድሜህ ነው
-ነጭና ጥቁር አይጦች ደግሞ ቀንና ማታ እድሜህን እየበሉብህ ነው ብሎ ሸኹ ነገረው። ያሸኽ ማሩስ ምንድነው ?!ሲል ጠየቀው
-ሸኺም ማሩማ ዱንያ ነች ጥፍጥናዋ ሞት ሂሳብ እንዳለብህ አስረሳችህ ብለው አሉት። ሱበሃን አላህ
👆ያጀመዓ በደንብ አንብቡት ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ሼር በማድረግ ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ይተባበሩ።
1
1
1August 27, 2026 198