ጸሎቱ እንዳለቀ ግራ ተጋቡ ጌታን አታውቅምኮ አሉት እጁን በአፉ አድርጎ ቆሞ ቀረ እኔ ግራ ገባኝ ምን እንደሚሉም አልገባኝም እንባዬን እየጠራረኩ እያፈራረኩ አየዋቸው አገልጋዩም ቀጠል አድርጎ ለወጋችን ቢሆንም ጌታን ትቀበያለሺ አለኝ? ዞር ብዬ ወደነሱ ተመለከትኩ ውስጤ ባማላውቀው ደስታ እና ድል ተሟልቷል እንቢ ለማለት አቅም አጣሁ በደስታ እሺ አልኩ ።
በደስታ ጮሁ አለቀሱ ገረመኝ ሆ እኔ ግን ጴንጤ አልሆንም አልኩ በልቤ 🤣🤣 ሞቻለኋ ብሞታት አይነት🤣🤣🤣 ብቻ እጄን አንስቼ ጌታን ተቀበልኩ ነፍሴ ታደሠች ወገኖቼ ለሊቱ ሙሉ በዓየር ሲሄድ አደርኩ ደስታ !!! ደስታ !!!! ደስታ !!! ማቋረጥ አልቻልኩም በነጋታው ጠዋት ወደ ቤቴ ሄድኩ የማያቋርጥ ዝማሬ እና ደስታ "እጄን ይዘህ አንተ ስትመራኝ ለራስህ አለማ ስትለየኝ ኡኡኡኡኡኡ ደስታ ደስታ የማያቋርጥ ደስታ "ያሻገረኝ ጌታ ያን የትናንቱን " ግን እናዛ ዝማሬዎች የት ሄዱ?😭😭😭
ቅዳሜ ለእሁድ ጠዋት ወደቸርች ልሄድ ለሊቱ ሙሉ ስሰቃይ አደርኩ ውሸታቸውን ነው መረጃ ሰብስበው ነግረውት ነው እህቶችሺስ? አባትሺ?እናትሺ? ተሸወድሺ እያለ ሲያሠቃዬኝ አደረ ። ፈራሁ ይቅርብሺ አትሂጂ ጴንጤ ልትሆኚ ነው? እመቤቴን ልትተይ? ስሰቃይ አን ዴ ሲያንጠለጥለኝ አንዴ ሲለቀኝ እንዳይነጋ የለ ነጋ ። አነጋጉ ላይ የወሰደኝ እንቅልፍ ስነቃ መልካም ነህ ለእኔ አባቴ በሚል መዝሙር ታጅቤ ነቃሁ።❤ " ይሁንልኝ ብዬ የተሟገትኳቸው"😭😭😭 ተነስቼ እንደምንም ብዬ እራሴን ታግዬ ደህና ልብስ ስሌለኝ🤣 ጥቁር ቱታ በነጭ ስትራይፕ በነጭ ቲሸርት በጥቁር ነጠላ ጫማ አድርጌ በደስታና በታላቅ ፍርሃት ተደብቄ ብቻዬን ሜጋ አካባቢ ወደሚገኝው ወደ ተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያን ሄድኩ የመጨረሻ ማረጋገጫ እግዚአብሔር አንተን እፈልጋለሁ አንተ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ከሆንክ ምልክት ስጠኝ...........................
እንደጌታ ፍቃድ ይቀጥላል
✍መማር
August 11, 2024 808 1