ኃጢአት ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ ይገልጣል
በቅዳሴ መጽሐፋችን ውስጥ እንዲህ የሚል የንስሃ ጸሎት ይገኛል፤"I acted if God did not matter." ይህ በጣም ትክክለኛ የኃጢአት ልምምድ አገላለጽ ነው።
በኃጢአት መመላለስ ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ ያሳያል። መስበክ፣ መዘመር፣ መጸለይና መንፈሳዊ ቋንቋዎችን መናገር መቻላችን ብቻውን ለእግዚአብሔር ያለንን ቦታ አይገልጥም። እግዚአብሔር በእኛ ዘንድ ያለው ቦታ እኛ ለኃጢአት ያለንን ንቀት ያህላል።
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:2-5, 8 አማ54
[2] በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። [3] ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ [4-5] ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤
[8] እንግዲህ የሚጥል ሰውን የጣለ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።
በቁጥር ስምንት ላይ "የሚጥል" ተብሎ የተተረጎመው የግሪኩ ቃል "የሚቃወም፣ የሚሽር" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው ይህንን የቅድስናን ጥሪ መግፋት እግዚአብሔርን መሻር ነው።
የኃጢአት ልምምድ እኛን ሊቀድሰን በውስጣችን እየሰራ ካለው ቅዱስ መንፈስ በተቃርኖ መቆም ነው፤ ኃጢአትን ሊያስወግድ የተገለጠውን ጌታ መናቅ ነው።
ነገር ግን ድካማችንን አምነን፣ በተሰበረ ልብ ወደ ፊቱ ብንቀርብ የሚያስፈልገንን ጸጋና የሚቀድሰንን መንፈሱን ሊሰጠን የታመነ አባት አለን።
@Romans148