ሃብልን የሚተካው የስፔስ ቴሌስኮፕ የመጨረሻውን ሙከራ ሊያደርግ ነው
=====================
በሰው ልጆች የጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሃብል ቴሌስኮፕ ወደ ጠፈር የመጠቀው እ.ኤ.አ በ1990 ሲሆን ጋሊሊዮ ከሰራት የመጀመሪያዋ ቴሌስኮፕ ቀጥሎም ለጠፈር ሳይንስ ምጥቀት ትልቁን ድርሻ ያበረከተ ግኝት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ መረጃዎች እንደሚሳዩት ሀብልን በመጠቀም ብቻ እስከዛሬ ከ14,000 በላይ ሳይንሳዊ ጥናቶች በተለያየ ዘርፍ ተደርገውና ታትመው ለአንባቢዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ይህም በሳይንሱ ዓለም በየትኛውም ዘርፍ ለሚደረጉ ጥናቶች ትልቅ መረጃን በማቀበልና በተለይም ለህዋ ሳይንስ እድገት ትልቁን አበርክቶት በበዋወጣት በዘርፉ ከተፈጠሩ ቴክኖሎጀዎች ከፊት ለፊት እንዲቀመጥ ያደርገዋል፡
ለ31 ዓመታት ዩኒቨረስን በመቃኘትና በትንሹ 1.2 ሚልዩን የሚሆኑ የጠፈር እይታዎች (observations) በማድረግ ለህዋ ምርምሩ ትልቅ ሚና የተጫወተው ሃብል የስፔስ ቴሌስኮፕ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጋጠሙት ባሉ ቴክኒካል ችግሮች እና ዘመናዊው የህዋ ምርምር የሚፈልገውን ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ግብዓት ያካተተ ባለመሆኑ አሁን በመሰራት ላይ ካሉት እንደ ጀምስ ዌብ ካሉ ሱፐር ቴሌስኮፖች አነስተኛ አገልግሎት እንዲኖረው ደርጉታል፡፡ ሃብል እሱን ተክቶ እየመጣ ካለው ጀምስ ዌብ የስፔስ ቴሌስኮፕ አንጻር በብዙ ዘርፎች አነስተኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ቢችልም በየጊዜው በሚደረጉለት ጥገናዎችና ማሻሻያዎች ቀድሞ ሲሰራ የነበረውን በአነስተኛ ሞገድ የጠፈር እይታዎች የማካሄድ እና ልዩ ልዩ መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራውን ሊቀጥል ይችላል፡፡
በ10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባተው ተጠናቆ ወደመጨረሻው ምዕራፍ የተሸጋገረው ጀምስ ዌብ ሱፐር ቴሌስኮፕ ሃብል ሲሰጠው የነበረውን አገልግሎት ከማቅረብ ባለፈ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የህዋ ምርምር ዘርፉንና አጠቃላይ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ይበልጥ የመሻሻል አቅም እንደሚኖረው ይነገርለታል፡፡ ወደምህዋር በገቡ የስፔስ ቴሌስኮፕች ታሪክ 6.5 ሜትር ርዝመት በመያዝ ግዙፍ የአስትሮኖሚካል ሚረር ወይም መስታዎት ካላቸው ቴሌስኮፕች ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፈው ይህ ቴሌስኮፕ በተለይም በረጅም የሞገድ ርዝመት እስከዛሬ ሊደረስባቸው ያልቻሉ የጠፈር እይታዎችን በማከናወን አዳዲስ እውነታዎችን ሊገልጥ መቻሉ ጀምስ ዌብን ለየት እንዲል ያደርገዋል፡፡
አሁን ላይ ይህ የስፔስ ቴሌስኮፕ በታህሳስ ወር ለሚያደርገው ወደ ህዋ የመወንጨፍ ፕሮግራም ደቡብ አሜሪካ በሚገኘው ፍሬንች ጊያና ማረፊውን ያደረገ ሲሆን ወደ ህዋ ከመጓዙ በፊት በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት የመጨረሻውን ፍተሻና አጠቀላይ የማጣራት ሂደት ኮርዋ ስፔስፖርት በተባለው የአውሮፓ ኩባንያ የሚደረግለት ይሆናል፡፡ በካናዳ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የስፔስ ኤጀንሲዎች ትብብር አጠቃላይ ስራው ሲከናወን ቆይቶ ወደመጨረሻው ምዕራፍ የተሸጋገረው ጀምስ ዌብ ሱፐር ቴሌስኮፕ ከሃብል የጠፈር እይታዎች ከ10 እስከ መቶ አጥፍ የላቀ ኦብዘርቬሽን በማድረግ ከ13 ቢሊዮን የብርሃን ዓመት ርቀት ላይ የሚታዩ ብርሃኖችን የመለየት አቅም አንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡
ቢቢሲ
https://www.bbc.com/news/science-environment-58888302

Bbc
James Webb super-telescope arrives at launch site
The successor to the Hubble Space Telescope reaches French Guiana to prepare for a December launch.
October 14, 2021 902 2