TechIn2: post #2922 — TG.ME

የዳሳሽ ማቴሪያሎች ጥቅምና አተገባበር
======================
ዳሳሽ ማቴሪያል (Sensor material) ማለት የዳሳሽ መዋቅራዊ ዘዴ ያለዉ ሆኖ የአከባቢን ሁኔታ ለምሳሌ የሙቀትን፤ የክብደትን፡ የግፊትን ስሜት ተረድቶ መልስ መስጠት የሚችል ማቴሪያል ነዉ፡፡ የዳሳሽ ማቴሪያል መዋቅር በዉስጡ የብርሀንና የእሳት ሙቀት መለኪያ፡ በሞተር የሚንቀሳቀሱና ኤሌክትሮኒክስን የያዘ ክፍል አለዉ፡፡ ይህ ዘዴ የአከባቢን ሁኔታ ተረድቶ መልስ መስጠት የሚችል አቅም እንዲላበስ ተደርጎ የሚሰራ ሲሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሰፊ አተገባበሮችን ሊወጣ ይችላል፡፡

ዳሳሽ ማቴሪያሎች ወጥነት ያላቸው ከመሆን ይልቅ ብዙውን ጊዜ ጥንቅር ማቴሪያሎች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ጥንቅር ማቴሪያል ማለት ደግሞ ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ቁሶች የተሰራ ማቴሪያል ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ ዳሳሽ ማቴሪያሎች ከተለመዱ የማቴሪያል አይነቶች በበለጠ መንገድ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን የራሳቸው የሆነ የአከባቢዉን ሁኔታ መቆጣጠር የሚችሉበት ዘዴ አላቸው፡፡ ለመሳሌ ያህል ክብደታቸዉ አነስተኛ መሆን፡ በቀላሉ በዝገት የማይጠቁና የተሰሩበት መዋቅር ጠንካራና ሊቆይ የሚችል በመሆኑ ነዉ፡፡ ባለንበት በ21ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ለብዙ አገልግሎት ይዉላሉ፡፡

በማቴሪያል ሳይንስ ዘርፉ ይበልጥ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው ይህ ዘርፍ ለአብነት በመኪና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዉስጥ ዳሳሽ ማቴሪያልን በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ለምሳሌ በመኪና ማምረቻ ዘርፍ ዉስጥ በማይክሮ ኤሌክትሮ መካኒካል ሲስተም ዉስጥ እንደ ስሜት ተረጂ ክፍል ሆኖ በማገልገል ኤርባግንና አንቲ ሎክ ያሉ የመኪና ማቆሚያ ዘዴዎችን ለመተግበርና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በሰፊው ሊያገለግል ይችላል፡፡

በዚህ ዘመን ከፍተኛ የሆነ የዳሳሽ ማቴሪያል ተፈላጊነት በገቢያ ዉስጥ በስፋት የሚገኝ ሲሆን ከመኪና ማምረቻ ዘርፉ በተጨማሪ በአዉሮፕላን የማምረትና የመገጣጠም ሂደት፣ የሰርጓጅ መርከብ፣ በባር ሃዲድ ግንባታ እና የመሳሰሉት ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊ ዳሳሽ መሳሪያን በመጠቀም በዘርፉ ያለዉን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ተችሏል፡፡ አሁንም ቢሆን በተለያየ የስራ ዘርፍች ላይ ምርምር በማድረግ የዳሳሽ ማቴሪያሎችን የበለጠ ተግባራዊነት መረዳት ይቻላል፡፡ ከዚህ ባለፈ ለምሳሌ ያህል በፒዞ ኤሌክትሪክ ፋይበር ጥንቅርና ቅርጻቸዉን በሚያስታዉሱ ፖሊመር ማቴሪያሎች ላይ ሰፊ ምርመሮችን እንዲደረጉ በማስቻል በህክምናዉ ዘርፍ ሳይቀር ወደፊት ብዙ ግኝቶች ሊያስገኝ ይቻላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://www.sciencedirect.com/.../enginee.../sensor-material
October 16, 2021 1.4K 3