ሊንክድኢን የቻይና ቅርንጫፉን ዘጋ
***********************************
ሊንክድኢን የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ በቻይና ያለውን አገልግሎት ማቋረጡን አሳወቀ፡፡ ይህ የማይክሮሶፍት ኩባንያ ንብረት የሆነውና የዘመኑ በተለይም በአሜሪካ ታዋቂ ከሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ውስጥ የሆነው የትስስር ገጽ በቻይና ምቹ የሆነ የስራ ከባቢ ባለመኖሩ በሚል ምክንያት አገልግሎቱን ማቋረጡን ይፋ አድርጓል፡፡
ሊንክዲኢን በቻይና ውስጥ 53 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ይህም ካጠቃላይ ተጠቃሚዎቹ ውስጥ 7 በመቶ የሚሆን እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ማይክሮሶፍት በቻይና በሚሰጠው አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ምን ያክል ገቢ ሊያጣ እንደሚችል ባይሳውቅም ተቋሙ አመታዊ ገቢው ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከፍ ማለቱን አሳውቋል፡፡
ማክሮሶፍት በቻይና ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ኢንጆብስ በተሰኘ የስራ ማፈላለጊያ ድረ-ገጽ ለመተካት ማቀዱንም ተናግሯል፡፡ በዚህ ድረ-ገጽም በሊንክድኢን ውስጥ ተካትተው የነበሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽታዎች እንደማይካተቱ ተሰምቷል፡፡ ይህም ማለት በቻይና ያሉ ተጠቃሚዎች ጽሁፎችንም ሆነ ምስሎችን ማጋራት አይችሉም፡፡
ማይክሮሶፍት ቻይና ተጠቃሚዎቼን በተለያዩ ምክንያቶች እያሳበበች መረጃዎችን እንዳይቀያየሩ እያደረገች ነው ሲል ከሷል፡፡ ለዚህም የተለያዩ የማህበረሰብ አንቅዊችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚያቀርቡትን ተደጋጋሚ የሆነ ክስ በማስረጃነት ተጠቅሟል፡፡
በዚህም የባይደን አስተዳደር ማይክሮሶፍት ቻይናን መከስሱንና አገልግሎቱን ለማቋረጥ መወሰኑን እንደወደደለት የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
ምንጭ ፋይናንሻል ታይምስ
ተጨማሪ ንባብ https://www.ft.com/content/bf56e388-f2c5-4686-90c0-b995529ce63f?fbclid=IwAR2G_iYeoHsZcAvyBAV7nVOBYkUhOOdJZMlziKbrhO_Knk6vpA-WL8BufrI
Ft
Subscribe to read | Financial Times
News, analysis and comment from the Financial Times, the worldʼs leading global business publication
October 16, 2021 1.9K 4