TechIn2: post #2911 — TG.ME

ሁለት ጭንቅላት እና ስድስት እግሮች ያሏት ኤሊ ተወለደች
=================
ከሁለት ሳምንታት በፊት በአሜሪካኗ የማሳቹሴትስ ግዛት ሁለት አንገት እና ጭንቅላት ያላት ኤሊ ተወልዷለች፡፡ ይህች መገኛው በአሜሪካን እና ቤርሙባ ከሆነ የዳይመንድባክ ቴራፒን ዝርያ የሆነችው ኤሊ ከሁለት ጭንቃላት በተጨማሪ ስድስት እግሮች ያላት መሆኗ ይበልጥ ትኩረትን እንድትስብ አድርጓታል፡፡

የኤሊዋ ሁለት ጭንቅላቶች ለየብቻቸው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ሁለቱን የሰውነት ክፍሎቿን ይመግቡላት ዘንድም ሁለት የምግብ ስርዓቶችን (gastrointestinal) ይዛ ነው የተፈለፈለችው፡፡

በግዛቱ ውስጥ የመጥፋት አደጋ ላይ ናቸው ከሚባሉ እንስሳት መካከል ከሆነው የኤሊ ዝርያ የተገኘችው ኤሊዋ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትገኝና ትላትል እና ሌሎች የቀረቡላት ምግቦችን እየተመገበች ስለመሆኑ አሁን የምትገኝበት በርድዜይ ኬፕ ዱርጥበቃ ማዕከል ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ኤሊዋ በቅድሚያ ከእንቁላሏ የተፈለፈለችበት ቦታ ለደህንነቷ መልካም የሚባል ባለመሆኑ ነው ወደ ማዕከሉ የተዛወረችው፡፡ የማዕከሉ እንስሳት ሀኪም ፒርላ ፓቴል ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ጤናዋን እየተከታተሏት ይገኛሉ፤ ኤሊዋንም በልጅነት ዕድሜያቸው እውቅናን አግኝተው በነበሩት መንትያ አሜሪካዊያን ተዋንያን ሜሪ ኬት እና አሽሊ ኦልሰን ስም ሰይመዋታል፡፡ ሀኪሞቹ በቀጣይም ስለ ኤሊዋ የደም ዝውውር ስርዓት የበለጠ ለመረዳት የሲቲ ስካን ምልከታን ለማድረግ አቅደዋል፡፡

ምንጭ፤ አሶሼትድ ፕረስ
ለተጨማሪ፤ https://apnews.com/article/oddities-massachusetts-turtles-wildlife-animals-3911b338a119295d443c3d909266dd96
AP News
2-headed baby turtle thrives at Massachusetts animal refuge
A rare two-headed diamondback terrapin turtle is alive and kicking — with all six of its legs — at the Birdsey Cape Wildlife Center in Massachusetts.
October 13, 2021 960