TechIn2: post #2909 — TG.ME

በክሊኒካዊ ሙከራው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው የካንሰር መድሃኒት
***********************************************
በተለምዶ አባ ጨጓሬ እያል ከምንጠራው የትል ዝርያ ከሚገኝ ፈንገስ የተለያዩ ሙከራዎችን አልፎ በተደረገለት ክሊኒካዊ ሙከራ ትልቅ ውጤት ያስመዘገበ የካንሰር መድሃኒት መገኘቱ ተነገረ፡፡ መድሃኒቱ በአባ ጨጓሬው ጥገኛ ሆኖ ከሚኖረው ሂማላያን የተሰኘ ፈንገስ የተዘጋጀ ሲሆን በተደረገው የደረጃ አንድ ክሊኒካዊ ሙከራ የካንሰር ህዋሳትን መግደል የሚችል መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም ውጤታማ የካንሰር መድሃኒት ለማዘጋጀት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ መሰረት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

መድሃኒቱ ኮርዲሴፒን ከተባለ በአባ ጨጓሬ ጥገኛ ሆኖ በሚኖረው ፈንገስ የሚመረት ውህድ የተሰራ መሆኑን ግኝቱ በተገለጸበት የክሊኒካል ካንሰር ምርምር መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡ አሁን ላይ ትልክ ተስፋ ከተጣለባቸው የካንሰር መድሃኒቶች መካከል የተካተተው በሌላ ስሙ 3'-dA በሚል የተሰየመው መድሃኒት ለዘመናት በቻይና ባህላዊ ህክምና ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ መድሃኒቶች ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያለው ነው፡፡

መድሃኒቱ በሙከራ ሂረት ውስጥ ካስመዘገበው ውጤት በተቃራኒው ጉድለቶችም ታይተውበታል፡፡ ከእነዚህም ዋነኛው በደም ስር ውስጥ በሚያደርገው ጉዞ የካንሰር ህዋሳትን እንዳያገኝ አዴኖሲን ዲያሜናስ (ADA) በተሰኘ ኢንዛይም ጥቃት የሚደርስበት መሆኑ ነው፡፡ በዚህም ጥቃት የተነሳ ራሱን ችሎ ወደካንሰር ህዋሳት መድረስ የማይችል በመሆኑ hENT1 የተሰኛ ድጋፍ ሰጭ ኒውክሎሳይድ ያስፈልገዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመሻገርም ተመራማሪዎቹ ፕሮታይድ የተሰኘ ቴክኖሎጂን መጠቀም መርጠዋል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በድሃኒቱ በደም ስር ውስጥ ወደ ካንሰር ህዋሳት በሚያደርገው ጉዙ ከሚደርስበት ጥቃት የሚከላከል ጋሻ ነው፡፡ በማሻሻያውም የተገኘው መድሃኒት የአዴኖሲን ዲያሜናስ (ADA) ጥቃት መቋቋም የሚችል በመሆኑ NUC-7738 የሚል ስያሜ ተሰጥጾታል፡፡

መድሃኒቱ በዋናነት የካንሰር ህዋሳት በደም ውስጥ እንዳይራቡ የሚያደርግና ሞታቸውን የሚያፋጥን በመሆኑ ተመራጭነቱና ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎቹ የመድሃኒቱን ሁለተኛ ዙር ሙከራ ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/anticancer-drug-derived-from-caterpillar-fungus-shows-huge-potential-in-clinical-trial/?fbclid=IwAR3oQu8pimSLMVGaQK0Ke-35031d6UlbbA2bhlrozrLXdwfGzyCGDJPL84w
IFLScience
Anti-Cancer Drug Derived From "Caterpillar Fungus" Shows Huge Potential In Clinical Trial
A molecule found in a parasitic Himalayan fungus has been found to kill tumor cells in a Phase I clinical trial, raising hopes that it may provide a founda
October 13, 2021 805 1