TechIn2: post #2907 — TG.ME

አዲስ ዓይነት የአውሮፕላን ነዳጅ ተሰራ
===============
ተመራማሪዎች የግብርና ተረፈ ምርትን በመጠቀም በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ሰሩ፡፡ ለተፈጥሮ በተሻለ ተስማሚ ነው የተባለለት አዲሱ ነዳጅ አሴቶን እና አልኮልን በማቀላቀል የተሰራ ነው፡፡

የተሻሻሉ ባዮፊውሎች ለከባቢ ተስማሚ ከሆነ ባዮማስ የሚመረቱና ከሌሎች ነዳጆች አንፃር አነስተኛ የበካይ ጋዝ ልቀት ያላቸው ነዳጆች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ረገድ አዲሱ ነዳጅ የተሻሻሉ ባዮፊውሎችን አስመልክቶ የተቀመጡ ደረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም ለደረጃዎቹ የቀረበና ጥቂት ስራዎች ከተሰሩበትም ተግባር ላይ መዋል የሚችል ነው፡፡

ከግብርና እና ምግብ የሚመነጩ ተረፈ ምርቶች አንዳንድ የተፈጥሮ ተስማሚነት መስፈርቶችን አሟልተው ከተገኙ ለተሻሻለ ባዮፊውል ምርት ግብዓት ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡ ይህ የባዮጀት ፊውል ፕሮጀክትም ከተፈጥሮ ግብዓቶች የሚመረት የአውሮፕላን ባዮፊውል ነዳጅ ዋጋ እና የምርት ሰንሰለትን በመመርመር ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ውጤት ታድያ ከፍተኛ ርጥበት ያላቸው የግብርና እና ምግብ ተረፈ ምርቶችን ወደተሻሻለ የአውሮፕላን ባዮፊውል ምርትነት በመውሰድ የገበያ ሰንሰለትን ለመዘርጋት ሊረዳ ይችላል ተብሎለታል፡፡

በጥናቱ ጥቅም ላይ የዋሉት ግብዓቶች ድንችን ከማቀነባበር ስራ የተገኙ ፈሳሽ ተረፈ ምርቶች ናቸው፡፡ ግብዓቶቹን በመጠቀም አሴቶን፣ ቡታኖል እና ኢታኖልን ወይም በሌላ አጠራር ኤቢኢ ፈርመንቴሽን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ፈሳሽ ውጋጆች ለኬሚካላዊ ለውጥ ወይም ፈርመንቴሽን የተመቹ ቢሆንም ያን ያህል ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ ናቸው፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ላይ የነዚህ ሦስት ምርቶች ውህድ ከሃይድሮጅን ጋር ከተቀላቀሉ እና ኬሚካላዊ ንጠላ (Fractionation) ከተደረገባቸው በኋላ ወደ ሀይድሮ ካርበንነት ሊለወጡ ችለዋል፡፡ በጥናቱ ላይ በተደረጉ ሙከራዎች ነዳጁን በግብርና ተረፈ ምርት አማካኝነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ምርት ማስገባት እንደሚቻል የታየ ሲሆን በተፈጥሮ ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ተፅዕንዖ እንዲሁም ምጣኔ ሐብታዊ ሁናቴው ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡

በዚህ ጥናት ላይ ነዳጁን ለማምረት ጥቅም ላይ የዋለው የድንች ማቀነባበርያ ተረፈ ምርት ይሁን እንጂ ወደፊት ለገበያ የሚበቃ ነዳጅን ለማምረት ግን ከሌሎች የግብርና ምርቶችም የሚወጣ ተረፈ ምርትን በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-10-kerosene-bio-based-side-streams.html
Tech Xplore
Producing kerosene from bio-based side streams
Wageningen University & Research and its partners have developed a new type of aviation fuel that is produced using bio-based waste streams from the agriculture industry.
October 13, 2021 891 1