RN.05 - Channel: post #4857 — TG.ME

ጽንፈኛው የእስራኤል ሚኒስትር አወዛጋቢ ግግር ሌላ ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከተለ
~~~~~~
#RN05
.
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ከርሮ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የእስራኤል ጽንፈኛው የብሔራዊ ጸጥታ ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር በጋዛ ላይ የሰጡት ከባድ እና አወዛጋቢ አስተያየት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል።
.
ሚኒስትሩ በጋዛ ሰርጥ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ፦ «ሊኖሩ የማይገባቸው ሰዎች፤ እነሱ ሰዎችም አይደሉም!» ማለታቸው ከፍተኛ አዲስ ቁጣና ውግዘት አስከትሏል።
.
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና አለም አቀፍ ተቋማት እንደሚያስረዱት፣ የቤን-ግቪር አገላለጽ የፓለስታናውያንን ሰብአዊነት ሙሉ በሙሉ የሚክድ እና የዘር ማጽዳት ወንጀልን የሚያበረታታ አደገኛ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነጸብራቅ ነው።
,
ጽንፈኛው ሚኒስትር በጋዛ ላይ የሚወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና የክልሉ ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ለማሳየት የሞከሩባቸው ሐረጎች በሰላም ድርድር ላይ ትልቅ ጥላ አጥልተዋል።
.
ይህ አባባል የእስራኤልን መንግሥት የውጪ ግንኙነት አቋም የበለጠ አስቸጋሪ ያደረገው ሲሆን፣ የጺዮናዊትዋ አፓርታይድ እና የጦር ወንጀለኞች ሃገር የሆነችው የእስራኤል አጋር ሀገራት ጭምር በንግግሩ ላይ ያላቸውን ጽኑ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ።
.
ተንታኞች እንደሚሉት፣ በኃተታ የተሞሉና የሰዎችን ሕይወት ዋጋ የሚቀንሱ እንዲህ ያሉ ጽንፈኛ መግለጫዎች በቀጣናው ያለውን ዘላቂ ሰላም እና መፍትሔ እጅግ አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ።
.
የብሔራዊ ጸጥታ ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር በጽንፈኛ አቅዋማቸው የሚታወቁ ሲሆን ብዙ አለም አቀፍ ህጎች ጋዛ ዉስጥ የጦር ወንጀል ለመፈጸሙ እንደማሳያ ከሚጠቀሱ የእስራኤል ባለስልጣናት መካከል ከዋነኞቹ ይመደባሉ፡፡ በቅርቡ በእስራኤል ዉስጥ ያሉና ፍልስጤማዊያን በብዛት የታሰሩበት እስር ቤት ዙርያው በአዞዎች እንዲከበብ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
.
የእናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል?? ?
የእናንተን እይታ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!
=============
.
ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ተቀላቀሉ
https://t.me/RNZeroFive
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍4
August 16, 2026 367 2 1