"ለመለወጥ መሞከር ትልቁ ስህተትህ ሊሆን ይችላል?"
"ያለውን እውነታ" (What is) አለመቀበል
አንድን ነገር ለመለወጥ ስንሞክር፣ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ወይም የራሳችንን ማንነት (ለምሳሌ፡ ቁጣን፣ ፍርሃትን ወይም ስግብግብነትን) እየሸሸን ነው ማለት ነው። አእምሯችን "መሆን ስላለብን" ነገር (What should be) ምናባዊ ምስል ይፈጥርና አሁን ካለንበት እውነታ ጋር ያጋጨናል። ይህ በነባራው እውነታና በምኞት መካከል የሚፈጠር ግጭት ደግሞ ውስጣዊ ሰላምን ያሳጣል።
በለውጥ ስም የሚመጣ ክፍፍልና ትግል
"የሚለውጠው አካል" እና "የሚለወጠው አካል" ብሎ አእምሮ ራሱን ለሁለት ይከፍላል። ለምሳሌ፡- ቁጡ የሆነ ሰው "ቁጣዬን ማጥፋት አለብኝ" ብሎ ሲታገል፣ ትግሉ ራሱ ሌላ የሃይልና የውጥረት መገለጫ ይሆናል። በሃይል ወይም በግዴታ የመጣ ለውጥ እውነተኛ ሳይሆን፣ ጭቆና ወይም ሌላ የአእምሮ ማታለያ (Suppression) ነው።
እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው እንዴት ነው? እውነተኛ ለውጥ(Transformation) የሚመጣው ለመለወጥ ከመታገል ሳይሆን፣ ያለፍርድ በጥንቃቄ ከመመልከት (Choiceless Awareness) ነው።
አሁን ያለህን ስሜት ወይም ባህሪ ሳታደንቅ፣ ሳትኮንን ወይም ለመለወጥ ሳትጣጣር ዝም ብለህ ስታስተውለውና ሙሉ በሙሉ ስትረዳው፣ ያ ባህሪ በራሱ ጊዜ መሟሟትና መለወጥ ይጀምራል።
🖤🖤🖤🖤🔉🔉🔉🔉🔉
#Jiddu_Krishnamurti










