NVIDIA Hugging Face ኩባንያን በ12.93 ቢሊዮን ዶላር ሊገዛ ነው
የቴክኖሎጂው ግዙፍ NVIDIA በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሶፍትዌሮች ልማት የሚታወቀውን "Hugging Face" የተሰኘውን ድርጅት በ12.93 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት መስማማቱን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጄንሰን ሁዋንግ አስታውቀዋል። ይህ ግዢ NVIDIA በAI ሃርድዌር ዘርፍ ያለውን የበላይነት ወደ ሶፍትዌርም ለማስፋት የሚያደርገው ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።
"Hugging Face" ከ18 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉትና የAI ሞዴሎችን በነጻ ለማጋራት የሚያገለግል እንደ "GitHub" ያለ ትልቅ መድረክ ነው። ጄንሰን ሁዋንግ መድረኩ ለሁሉም የAI ተመራማሪዎችና አልሚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥልና ተጠቃሚዎች የንቪዲያ ምርቶችን ብቻ እንዲጠቀሙ እንደማይገደዱ ቃል ገብተዋል። ይህ ስምምነት በዘርፉ ያሉ ክፍት የሶፍትዌር ምንጮችን (open-source AI) ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

September 4, 2026 9