የአፕል (Apple) ኩባንያ ታሪካዊ የሊደርሺፕ ለውጥ ይፋ ተደረገ!🍏🔥 የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ (CEO) የሆኑት ቲም ኩክ (Tim Cook) ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን እና አዲሱ ተተኪያቸው ይፋ መደረጉን የአፕል ቦርድ በይፋ ተረጋግጧል። ይህ ታሪካዊ ሽግግር በሚቀጥለው ሳምንት September 1, 2026 በይፋ ተግባራዊ ይሆናል። ቲም ኩክ እ.ኤ.አ በ2011 ከስቲቭ ጆብስ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ኩባንያውን ለ15 ዓመታት በስኬት መርተዋል። ከCEOነታቸው ቢለቁም የአፕል የቦርድ ሊቀመንበር (Executive Chairman) በመሆን ስራቸውን ይቀጥላሉ። በዚህም እስካሁን የአፕል የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ተርነስ (John Ternus) ሙሉ በሙሉ የCEOነቱን ቦታ ይረከባሉ።ጆን ከ2001 ጀምሮ በአፕል ውስጥ የቆዩ ሲሆን፣ ማክ (Mac) እና አይፎን (iPhone) ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ምርቶችን በመስራት ትልቅ ሚና የነበራቸው አንጋፋ መሃንዲስ ናቸው።
August 29, 2026 38