Jonathan Tutorials: post #78 — TG.ME

#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

‼️ በመጀመሪያ ብዙ የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት ⤴️

ለ2026 DV ለማመልከት »»»»»»»»»»»»»
https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለ DV የመረጡትን Photo ብቁ መሆኑን ለማወቅ »»»»»»»»»»»»»»»»
https://www.greencardphotocheck.com

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመልከቻው እስከ ህዳር 5
/2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በሚሞላበት ስፍራ መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም የ ' ልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩ ' ን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የሚጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን
dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

📪 Video  ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/qdwSvJJ2l_g?si=y6tZ54vLGKttjnOn

👆👆👆Share 👆👆👆Share👆👆
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🅾️ For Fast and Reliable info..⬇️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
         ⬇️ Join and Share ⤴️👇
      ╔═══════════╗
      ❇️
@JonathanTutorials ❇️
      ❇️
@JonathanTutorials ❇️
      ╚═══════════╝
October 11, 2024 2.1K 3 8