ሰበር መረጃ! በምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳዎች ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ያነሱ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች፣ በሲቪል… — Jema Insider — TG.ME

ሰበር መረጃ!

በምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳዎች ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ያነሱ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች፣ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መታሰራቸው ተገለጸ።

በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የውይይት መድረክ ላይ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሌሎች ቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም የነበራቸውና የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ ያቀረበውን አጀንዳ ለመቀበልና ለማስፈጸም አስቸግረዋል የተባሉ 300 የሚደርሱ ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት መታፈናቸው ታወቋል።

ከስፍራው ከተገኙ የዓይን እማኞች በተገኘው መረጃ መሠረት፣ የታፈኑት ተሳታፊዎች ከአማራ፣ ደቡብ፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የምክክር ኮሚሽኑ ተሳታፊዎች ናቸው።

የታፈኑት ተወካዮች በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ተወስደው መታሰራቸው ተረጋግጧል።

ይህ የሃይልና የእገታ እርምጃ የተወሰደበት ዋና ምክንያት አገዛዙ በምክክር ኮሚሽኑ በኩል ለማስጸደቅ ያቀደው የፖለቲካ አጀንዳ በእነዚህ ተሳታፊዎች በኩል ባጋጠመው ከፍተኛ ተቃውሞና እምቢተኝነት በመሰናከሉ እንደሆነ ተመልክቷል።

በተለይም ነገ በሚካሄደው የምክክር ኮሚሽኑ ምላተ ጉባኤ ላይ እነዚህ ጠንካራ ተቃዋሚ ተሳታፊዎች በሌሉበት አዲስ አበባን የኦሮሚያ የማድረግ አጀንዳን ጨምሮ የታቀዱ ውሳኔዎችን ያለተቃውሞ ለማሳለፍ ታስቦ የተፈጸመ መሆኑ ተገልጿል።

ድርጊቱ ኮሚሽኑ የአገዛዙን ፍላጎት ብቻ የሚያስፈጽም መሣሪያ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠ ክስተት እንደሆነ ተጠቅሷል።
❤7🔥1
August 18, 2026 354