ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የቴዎድሮስ ዕዝ የአመራር ሪፎርም መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የቴዎድሮስ ዕዝ ላለፉት ወራት የአመራር ሪፎርም ለመስራት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሂደት ዕዙ መዋቅራዊ አንድነቱ ተጠብቆ ጤናማ ሽግግር እንዲያደርግ ሂደቱን በጥንቃቄ እና በትዕግሥት መምራት አስፈላጊ በመሆኑ በሚፈለገው መልኩ በፍጥነት ሳይጠናቀቅ ቆይቷል።
የአደረጃጀት ፈተና ከድርጅት ዕድገት ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚፈጠር ቢሆንም ከውጭ ወደ ውስጥ የሚሰነዘሩ ከፋፋይ ጥቃቶችን እየመከቱ ተፈጥሯዊውን ውስጣዊ ትግል ለመዋቅራዊ ዕድገት በሚጠቅም መልኩ ለማዋል በጥበብ የተመራ ትግል ተደርጓል።
ድርጅታዊ መስመርን ለማስጠበቅ የተሄደበት ውስጠ ድርጅታዊ አሰራር ተገቢ እና ትክክል መሆኑ የዕዙን መዋቅራዊ አንድነት አስጠብቆ ለላቀ ግዳጅ የሚያበቃ ውጤት ላይ እንዲደረስ አስችሏል።
ይህ የዕዝ አመራር ሪፎርም በተለያዬ ደረጃ ውስጥ ያለፈ እና የመዋቅሩ ተዋረዳዊ ተሳትፎ የነበረበት ነው። የዕዙ ስራ አስፈጻሚ የሪፎርም ስራ አፈጻጸም ሂሩት ላይ የዕዙ ተወካይ በሆኑ የፖሊት ቢሮ አባላት አማካኝነት የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል። ቀጥሎም ምክትል መምሪያ ሀላፊዎች እና ሌሎች የክፍል ሀላፊዎችን አወያየቷል። በመጨረሻም በነዚህ መድረኮች የተገኘውን ግብአት በመውሰድ የዕዙ ስራ አስፈጻሚ የሪፎርም ኮሚቴ እንዲዋቀር ወስኖ፣ የአወቃቀር ሂደቱ የሚመራበትን መመሪያ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል።
በዚህ መሠረት ከክፍለጦሮች፣ ከኮር እና ከምክትል መምሪያ ሀላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ በማዋቀር የሪፎርም ኮሚቴው ተመሰርቷል። የዕዝ ስራ አስፈፃሚው በሰጠው መመሪያ እና ስልጣን መሠረት የሪፎርም ኮሚቴው የዕዙን የአመራር ሪፎርም ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ስራውን ጨርሶ ፕሮፖዛሉን ለዕዙ ስራ አስፈጻሚ አቅርቧል። ስራ አስፈጻሚው የቀረበለት ፕሮፖዛል መነሻ አድርጎ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የኮሚቴው ፕሮፖዛል ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አድርጎ የዕዙን የአመራር ሪፎርም የመጨረሻ ዝርዝር አጽድቋል።
በዚህም መሠረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ - ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ቴዎድሮስ ዕዝ የአፋብን መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 60 ስር በተቀመጠው መዋቅር መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መልኩ ተደራጅቷል።
1) ሰብሳቢ:- አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን
2) ም/ሰብሳቢ:- አርበኛ ጎበዜ ጌታቸው
3) ወታደራዊ አዛዥ:- ሻለቃ የኔአለም ዘለቀ
3.1) ምክትል ወታደራዊ አዛዥ:- መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ
4)ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ:- አርበኛ ግሩም ምሳሌ
4.1) ምክትል:- አርበኛ አማረ ካሴ
5) ፅህፈት ቤት ኃላፊ:- አርበኛ ናትናኤል ስናማው
5.1)ምክትል:- አርበኛ ብዙነህ እምቢያለ
6) አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ:- አርበኛ እስቲበል አለሙ
6.1) ምክትል:- አርበኛ ደመላሽ አንድነው
7) የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ:- አርበኛ ወግደረስ ጤናው
7.1)ምክትል:- አርበኛ ታደሰ አስማረ
8)ጥናትና ስትራቴጂ ጉዳዮች መምሪያ:- አርበኛ ዳሞት አለኸኝ
8.1)ምክትል:- አርበኛ መንግስቱ አማረ
9)ፋይናንስ እና ግዥ አስተዳደር:- አርበኛ ይትባረክ አንዳርጌ
9.1)ምክትል:- አርበኛ ያሬድ በቀለ
10)የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ:- አርበኛ ዘመን ተሻለ
10.1)ምክትል:- አርበኛ በለጠ ልየው
11) ሴቶች ጉዳይ መምሪያ- ፋኒት አትጠገብ አጥናፉ
11.1)ምክትል:- ፋኒት ክብራለም አያልነህ
12) ማሕበራዊ ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ ላይችሉህ ገበየሁ
12.1) ምክትል:- አርበኛ በላይነህ አለምነህ
13) የሰው ሃብት -ዳኛው ሽባባው
13.1) ምክትል:- አርበኛ በረከት አጥናፉ
14)ት/ት እና ስልጠና መምሪያ:- አርበኛ ክንፈመላክ ካሳ
14.1)ምክትል:- አርበኛ ዘውዳለም አዱኛ
15) መካናይዝድ ጦር መምሪያ:- ኮሎኔል አደመ ልጃለም
15.1) ምክትል:- መቶ አለቃ ሳሙኤል አታላይ
16)ህግ እና ስነስርዓት መምሪያ:- አርበኛ ዘማርያም እስከዚያ
16.1) ምክትል:- አርበኛ ቻላቸው ታፈረ
17) ሀብት አፈላላጊ መምሪያ- አርበኛ ሀይለሚካኤል ባዬህ
17.1) ምክትል:- አርበኛ ደሴ ጌታሁን
18) እቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ:- አርበኛ የሻነው መለሰ
18.1) ምክትል:- አርበኛ አታላይ ሞሴ
19) ዘመቻ መምሪያ-አምሳ አለቃ ታደሰ ልንገሬ
19.1) ምክትል:- መቶ አለቃ አጃናው ጥላሁን
20) ሎጀስቲክ መምሪያ:- አርበኛ ይርሳው ደምስ
20.1) ምክትል:- መቶ አለቃ አስረስ ምህረቴ
21) ወ/አስተዳደር መምሪያ- መቶ አለቃ ያሬድ ጫኔ
21.1) ምክትል:- 50 አለቃ ይበልጣል መልካሙ
22)ወ/ስልጠና መምሪያ:- ሻምበል ጌትነት ንጉሴ
22.1) ምክትል:- አምሳ አለቃ ዘላለም ደሴ
23) ልዩ ዘመቻ መምሪያ- መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኜ
23.1)/ምክትል:- ሻለቃ በላይ ብዙ አየሁ
24) መረጃ - ----------
24.1) ምክትል-- --------
25)ኢንዶክትርኔሽን መምሪያ:- መቶ አለቃ ጊዮን ጀንበሬ
25.1) ምክትል- መቶ አለቃ ገረመው አጋዠ
26) ወታደራዊ እቅድ እና ስትራቴጅ:- ሃምሳ አለቃ ስማቼው ቢሻው
26.1) ምክትል:- መቶ አለቃ ለዓለም ጌታሁን
27) ወታደራዊ መረጃ------
27.1) ምክትል- -------
28) ጤና መምሪያ:- ዶክተር እንዳላማው ጤናው
28.1) ምክትል-- ዶክተር ደመቀ አያሌው
7
1July 26, 2026 551 1