‼️ #ብሶት የወለደው ወቅታዊ #ሆያ_ሆዬ‼️🙌
.
#መጣና በአመቱ፣
ኧረ እንደምን ሰነበቱ?
ሆያ ሆዬ ነው፣
የምንለው፣
ሆያ ሆዬ ጉዴ፣
ጦርነት ነው ልማዴ።
.
#የኢትዮጵያ_ህዝቦች /ሆ/ እንደምን ናቹ፤
ከአዲስ አበባ / ሆ/ መጣንላቹ፤
ሆ ስንል አመፅ /ሆ/ እንዳይመስላቹ😂
ሆያ ሆዬ ነው /ሆ/ የምንልላቹ።
.
ሆያ ሆዬ /ሆ/ ሆይ የኔ ጌታ /ሆ/ ጌታ ጠንበለል ፤
ድሮኗ መጣች /ሆ/ ወዴት ልጠለል😂
ቤት መኖርያዬ/ሆ/ ተደረማምሷል፤
የዘር ጥላቻ /ሆ/ በአንድነት ፈርሷል፤
ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ /ሆ/ የት ይደረሳል።😄
ሆያ ሆዬ ጉዴ፣
ማፍረስ ነው ልማዴ፣
.
#የኛማ_አብይ "ሆ/ ጥርሰ በረዶ፣
የማይናደፍ "ሆ" ከንብ ተወልዶ፣
በለውጥ ሰበብ /ሆ/ሲገድለን ስንቱ ፣
ወንጌል ይመሥል ሆ/ ህገ መንግስቱ😂
ምህረት ፍቅር ነው ሆ/ ሁሌም ቃላቱ፣
ብለን ስናማው "ሆ" ንቀን ስናየው፣
ጭስ ሆኖ መጣ /ሆ / ንብ ላሰቃየው፣
በጭስ አፍኖ ገደለን ወየው😂
ሆያ ሆዬ ነው የምንለው...
እዛ ማዶ ሆ እሳት ይነዳል፣
እዚህ ማዶ ሆ ቦንብ ይፈነዳል፣
ድሮኗን ያየ /ሆ/ ዓለም ይፈርዳል፣
እንኳን ወታደር/ሆ/ ህዝብ ያሳድዳል።
“ዓመት ዓውደ አመት /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ኢትዮጵያ ሀገራችን /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ምድራዊ ገነት /ድገምና/ አመት /ድገምና/
ከሲኦል ተላቃ /ድገምና/ አመት /ድገምና /
ሰላም ይብዛላት /ድገምና/ ዓመት ድገምና
ፍቅር ይፍሰስባት "ድገምና" አመት /ድገምና /
አመት ድገምና
አመት ድገምና
ዓመት ድገምና
ድገም በስንዴ ድገም በጤፍ
ጠላቷ ይርገፍ
እንሾሽላ ፍሬ እንደቆላ ጤፍ።
ድገም በስንዴ ድገም በጤፍ
ከማንም ከምንም ኢትዮጵያ ትግዘፍ!!!!!

