የረቢዕ ነገር አጂብ ነዉ ወላህ! በወር መጠሪያነት፣ በወቅት ስያሜነት አሊያም በቀናት ቁጥር ወሰን ውስጥ ብቻ ተገድቦ መቅረት ፈፅሞ ይከብደዋል፤ ማዕረጉም፣ የከፍታው ልክም በዚሁ አይወሰንም። የብራማነቱ ብርሃን የልብን ጥልቅ ጉድጓዶች እያበራ የትካዜን ጥላ ይገፋል፤ መንፈስ አዳሽ የሆነው መዓዛው ደግሞ የደከመችን ሩህ በወኔ ይቀሰቅሳታል።
የውበቱ ድንበር የለሽነት አዕምሮን በወሰን የለሽ ምናብ ውስጥ ሽምጥ ያስጋልባል፤ የአንድምታው ጥልቀት የሰው ልጅን አስተሳሰብ የሀሳብ ማዕበል ውስጥ ያባክናል። እንዲህም ነው... እንዲያም ነው... እያሰኘ የውስጣችንን ስሜት በሙሉ ያብከነክነናል፤ ህሊናችንን በስሜት ውቅያኖስ ይነክሰዋል። ስለ እርሱ በርካታ ነገሮችን ማለትን፣ በወርቅ ብዕርም የልብን ትርታ መክተብን ያስመኛል።
ልክ እንደ ያኔው የታሪክ ማዕዘን፣ ልክ እንደ መላው ዓለማቱ ታላቁን የራህመት ብስራት እንደመጠባበቅ ሂደት ውስጥ መንፈስን በፍቅር ይደባልቃል። የውስጥ ጉጉትን አስቀድሞ በልብ ጓዳ ውስጥ በናፍቆት እሳት ይንጣል። ለዚህ የብርሃን ማዕበል መድረስ ለዚህም ፀጋ መታጨት መታደል ነዉ። ይህ ሁሉ እኮ ከረቢዕ በረከት የሚቀዳ ነው።
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐላ ኸይሪል አናም፣ ወዐላ አሊሂ ወሶህቢሂ አጅመዒን!
t.me/IbnuHashm















