❗ፌሚኒዝም እና የሴት ልጅ ጥቃት
ሰሞኑን እየሰማናቸው ካሉት በሰዎች ላይ ከሚፈፀሙት ዘግናኝ ነገሮች ዉስጥ የሴት ልጅ ጥቃት አንዱ ነው ይህ ጥቃት የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ፔይኑን ፊል የሚያደርጉት ወይም የወለደች, በዛ journey ያለፈች በእድሜ የበሰለ ሰዉ ተብሎ limit የሚደረግ ነገር አይደለም!
ሴትን ልጅ መድፈር ሕፃንም ትሁን ትልቅ ምንም ነገር ሊያባብለው የማይቺል አካላዊ ስቃይ ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ psychologically ጉዳት የሚያደርስ ነው!
ይህንንም ነገር ደግሞ አንድ ሴት ወይም social media ላይ ያሉ content ክሬተሮች, ኡስታዞች,ፌመስ ሰዎች ብቻ የሚጮሁለት ጉዳይ ሳይሆን ሙሉ ዜጋን የሚመለከት ሁሉንም ቤት የሚያንኳኳ እንደሀገር ዝም ሊባል የማይገባ በቶሎ እልባት የሚያስፈልገው ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ነው!!
ይሄንንም አሰቃቂ የ እንሰሳ ድርጊት ዛሬ ዛሬ social media መጣና ይበልጥ እየሰማን መጣን እንጂ መደፈር ብቻ ሳይሆን,አካላዊ ጥቃት ማድረስ,ግድያ, እነዚህ ተግባራቶች የቆዩ ብዙ ቤቶችን የዳሰሱ ብዙ እናቶቺን ያለልጅ ያስቀሩ, ገና አካላቸው ያልጠኑ ሴቶች በስትክክል የወር አበባ ማየት ያልጀመሩ እሕቶቻቺን ልጆቻቺን በ ፊስቱላ ተሰቃይተው የሞቱበት even መጥፎ በሺታዎቺን ጭምር ተይዘው ሕይወታቸውን ያጡ እንስቶችን ቤት ይቁጠራቸው በ ጫካው ተገለው የሚጣሉትንም ጭምር ደም ያጨቀየው ቀዬ አፍ ኖሮት መስክር ቢባል በተርገፈገፈ ነበር ::
💥ይህንን ሁሉ ስቃይ እና መከራ ተፈራርቆባቸው ለሞቱት ሕፃናት ልጆቻቺን እሕቶቻቺን ብሎም ላልሞቱ እያሳለፉ ላሉት በሙሉ ድምፅ መሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው የ ወንድሞች ኡስታዞች የስልጣን ወንበር ያሞቃቸው ፖለቲከኞቻቺን, ህዝብን የሚመራው ባለስልጣን ሳይቀር ግዴታ ጭምር ነው!!
ለዚህም ተመጣጣኝ ቅጣት እነዚህን ጨካኞች ባደባባይ ተመጣጣኝ ቅጣት ከመጀመሪያዉም ቢኖር እሕቶቻቺን ልጆቻቺን ባልተደፈሩ, ባልተገደሉ ባልተሰቃዩ ነበር!!! በሸሪአ አለመተዳደር የሚያመጣው አንዱ ቺግር ይህና መሰል ናቸው