ኡስታዝ ባህሩ ተካ በዑለማዎቻችን የአቋም መግለጫ ላይ የሰነዘርከውን ትችት ቆም ብለህ ብትመለከተውና ብትታረም መልካም ነበር!!
—————
ፅሁፍህን እንዳነበብኩት መልስ ለመፃፍ ወስኜ በ2 ምክንያቶች ለማዘግየት ሀሳቤን ቀየርኩ፣
1ኛ, ዑለማዎች ራሳቸው መልስ ይሰጡበታል በሚል ነበር፣ ለምን እንዳዘገዩት ራሳቸው ያውቃሉ… በነሱ በኩል መልስ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ላይታያቸውም ይችላል፣ አለያም ጊዜ ጠብቀውለት ሊሆን ይችላል…ወዘተ።
2ኛ, ፅሁፍህ ፍፁም ትክክል አለመሆኑን ተረድተህ ስትረጋጋ በእራስህ ጊዜ መልስ ትሰጣለህ ብዬም ተስፋ አድርጌ ነበር። ይህም አልሆነም።
በእራስህ ጊዜ እርማት እስካላደረግክ ግን በአደባባይ የተሳሳተን ሰው በአደባባይ እንዲታረም ምላሽ መስጠትና ብዥታን ከሰለፊይ ወንድምና እህቶች የመግፈፍ ግዴታ አለብን!!
ኡስታዝ ባህሩ እኔንም አንተንም አላህ በሐቅ ጎዳና ያፅናንና "በአቋም መግለጫው ላይ የማነሳቸው ነጥቦች" በሚል ርእስ የፃፍከው ፅሁፍ እጅግ ከእውነት የራቀ ለመሆኑ የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት:-
①, በፅሁፍህ መንደርደሪያ ላይ "ከሀገራችን የሰለፍይ መሻኢኾች ውስጥ የተወሰኑት…" በማለት የሰጡትን መግለጫ የውስን መሻይኾች እንጂ አንድነት የሌለውና መሻይኾችም ላይ የሆነ ልዩነት የተፈጠረ አስመስሎ የማቅረብ ዘይቤ ተጠቅመሃል፣ ይህ ትልቅ ስህተት ነው!! ቢታረም መልካም ነው።
②, አስከትለህም "…በዐረብኛውና በአማርኛው ትርጉም መካከል የተወሰኑ ልዩነቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ በዐረብኛ የተወሰኑ ዑለሞች የሚለውን በአማርኛ ዑለሞች ተብሎ ተተርጉሟል።" ብለሃል፣ ዐረቢኛው ላይ
لعدد من علماء السنة
በሚል ነው የተቀመጠው፣ ይህ ደግሞ ትርጉሙ አንተ እንደምትለው "ከፊል ዑለማእ" ወይም በዐረቢኛው
بعض العلماء
ማለት ሳይሆን!፣ ትክክለኛው ትርጉሙ " ከ3 በላይ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሱንና ዑለማዎች" ማለት ሲሆን ብዙሃነትን ገላጭ ነው።
በዚህ ቃል ከመተቸትህ በፊት ዐረቢኛው ሀሳቡ ግልፅ ካልሆነልህ የተለያዩ የዐረቢኛ ማብራሪያዎችን ብትመለከት መልካም ነበር፣ እኔም በዚህ አገላለፄና ትሩጓሜ ከተሳሳትኩ በዘርፉ ላይ ከአንተም ከኔም የተሻለ አቅምም ብቃትም ያላቸው ከኡስታዝ እስከ ታላላቅ መሻይኽ አሉን ያርሙናል ስህተት ከሆነም በበኩሌ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ!!።
በመሆኑም በዚህ መሰረት አማርኛው "ከሱንና ዑለማዎች የተሰጠ መግለጫ" ከሚለው ይልቅ ዐረቢኛው ላይ የተቀመጠው ይበልጥ ብዙሃነትን ገላጭ ነው እንጂ ምንም አይነት የትርጉም ልዩነት አልለ ሊያስብል የሚችል አይደለም!!። ቀጥታ ሲተረጎም ስለሚሰፋ የአማርኛውን ቀለል ባለ መልኩ ተመሳሳይ ብዙሃነትን ገላጭ ቃል ተጠቅመዋል እንጂ ምንም የትርጉም ልዩነት የሚፈጥርና የሚያስተች ነገር የለውም!!። ይልቁንም በተቃራኒው ትችቱን ራሱ በስህተት ላይ የተመሰረተ አድርጎታልና ታረም!!።
③, ሌላው ከባዱና ዐይን ያወጣ ውሸት የሚመስል ነገር ደግሞ ቁ,1 ብለህ ያስቀመጥከው ነጥብ ላይ "…ይሁን እንጂ የተገኙት እኔ በማውቀው ከሀገራችን የሱና ዑለሞች ውስጥ ግፋ ቢል 1/3 የሚሆኑት ናቸው። ስብሰባው ተነግሯቸው በዑዝር ምክንያት የቀሩና ያልሰሙም በጣም ብዙ ናቸው።" ማለትህ ነው። እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልፅ ብታደርግ መልካም ነበር… እርሱም #ከዚህ_በፊት የዑለማዎችን ጉባዔ የሚሳተፉ የነበሩት #ዑለማዎች (መሻይኾች) አጠቃላይ ብዛታቸው ስንት እንደነበረና በአሁኑ ጉባዔ (ሹራ) ላይ ምን ያህሉ እንደቀሩ ግልፅ አድርገህ ብትኮንን ጥሩ ነበር። የሚያሳፍረው የተገኙት መሻይኾች "…ግፋ ቢል 1/3 የሚሆኑት ናቸው" የሚለው ነው። ይህ ማለትኮ እንደ ፅሁፍህ አቀማመጥ ለምሳሌ 9 መደበኛ ተሰብሳቢ መሻይኾች ካሉ 3ቱ ብቻ ናቸው ተሰባስብው ተወያይተው መግለጫ ያወጡት ማለት ነው። አለያም ደግሞ 3 ወይም 4 የሚሆኑት ናቸው ተሰባስበው 2ቀን ሙሉ ተነጋግረው መግለጫ የሰጡት እያልከን ነው። ይህ ታዲያ ዐይን ያወጣ ግልፅ የሆነ ውሸት አይሆንም ወይ? ዐይን ያወጣ ውሸት የሚመስል ነገር… ያልኩበት ምክንያት ምን ያህል መሻይኾች እንደቀሩና ምን ያህሉ እንደተሳተፉ ልብህ ጠንቅቆ ያውቀዋል!!
= ለአንባቢያንና በመሻይኾች መካከል ልዩነት የተፈጠረ መስሏቸው ለተጨነቁ ወንድም እህቶች ግልፅ ለማድረግ ያህል፣ የቀሩ መሻይኾች እራሱም በዑዝር ምክንያት መቅረታቸውን እንደገለፀውም ነው፣ ነገር ግን ዋናው ነጥብ እሱ እንደሚለው "የቀሩት በጣም ብዙ ናቸውን?…" ትክክለኛው ቁጥራቸውስ ምን ያህል ነው? የሚለው ነው፣ #ከዚህ_በፊት_በነበሩ መደበኛ የዑለማእ ጉባዔዎች (ሹራዎች) ይሳተፉ ከነበሩት #መሻይኾች ይህ መግለጫ የወጣበትን ሹራ ያልተሳተፉት 2 (ሁለት) መሻይኾች ብቻ ናቸው። ታዲያ ቅጥፈትና ማምታታት አይሆንም ወይ?!! ባረከላሁ ፊክ፣ ባታውቅ ዑዝር እሰጥህ ነበር ልብህ እያወቀ ነው በዚህ መልኩ የፃፍከው።
④, ሌላው በቁ,2 ላይ እንደ ሀሳብ "… የአቋም መግለጫውን ላልተገኙት ልከው የሚጨመርም የሚቀነስም ካለ ሐሳብ እንዲሰጡበት አድርገው… " ብለህ ያስቀመጥከውም ሊሆን የማይችል ሀሳብ ነው። ምክንያቱም 1, እነዚህ በርካታ የተሰበሰቡ መሻይኾች ለ2 ቀናት ሲወያዩ በመስለሀና መፍሰዳው ሲያወጡ ሲያወርዱ የቆዩበትን ጉዳይ ያልተገኙት መሻይኾች የሆነ የተለየ ሀሳብ ቢሰነዝሩ እንደ አዲስ እንዲከፈት ሌላ ጊዜ የሚፈልግ ተግባር ነው። 2, ይህን መግለጫ ለማውጣት ብዙሃኑ ተገኝተው የወሰኑት ጉዳይ ስለሆነ ቀሪዎቹ የሚስማሙበት እንጂ ለክፍተት የሚዳርግ ጉዳይ ስላልሆነ። 3, በርካታው አባላት ውድ ጊዜያቸውን አቃጥለው ተሰባስበው በ2 ሰው መቅረት ምክንያት ተብሎ የሚደናቀፍ አሰራርም ሆነ የሚሻር ውሳኔ የለም!!። ይህ ያንተ ሰፋ አድርገህ ነባራዊ ሁኔታዎችን ሳታገናዝብ የሰነዘርከው ትክክለኛ ያልሆነ ሀሳብ ነው።
⑤, ዐሊ ሁሴንን በተመለከተ "…ከዛ በኋላም ቢሆን በዋነኝነት ከዛ በፊት ሲዘምተባቸው በነበሩ ሰዎች ላይ ውስጥ ለውስጥ ፊትናውን እስካሁንም እያሰራጨ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ያለ በመሆኑ አሁን የተሰጠው ምስክርነት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጋጭ ነው እላለሁ።" ብለሃል፣ እዚህ ላይም ከጠቀስከው አይቀር "ይህን ባህሪውን አልተወም" ብለህ ማስረጃ መጥቀስ ነበረብህ፣ ምክንያቱም በአደባባይ ግልፅ የሆነን ተውበት አድርጓል፣ ድምበር ያለፈባቸውንም ሰዎች አንተን ጨምሮ ይቅርታ ጠይቋል፣ መሻይኾች ግልፅ ባደረገው ነገር ነው ብይን የሚሰጡት እንጂ በልቡ ውስጥ ስላለው አይመለከታቸውም!፣ የውስጡን ወደ አላህ አስጠግተው ባደረጉት ክትትል ልክ ብይን ሰጥተዋል። አንተ ደግሞ ተውበት ካደረገ በኋላ ከማስተካከል ይልቅ ወደነበረበት ተግባር እየተመለሰ ነው ካልክ ሌላ ጊዜ እንደምታደርገው መሻይኾች ከመሰባሰባቸው በፊት ማስረጃህን መላክ ነበረብህ፣ አሁንም ግልፅ ማስረጃ ካለህ ለመሻይኾች ላከው፣ እራሱ ማብራሪያ ይሰጥበታል፣ መሻይኾችም ለማየት የሚከብዳቸው ነገር የለም። አለያ ግን በአደባባይ ከስህተታቸው ተውበት አድርገው የተመለሱ ሰዎችን የምንፈልገውን እያቀረብን፣ የማንፈልገውን ምክንያት እየደረደርን ከጀመዐህ ለማራቅ ጥረት የምናደርግ ከሆነ፣ የእኛም ልብ በአላህ እጅ ነው ያለውና ነገ ሰዎች የወደቁበት ስህተት ላይ ላለመውደቃችን ማናችንም ዋስትና የለንም!!፣ ሌላው:- ትላንትም እውነት በጥፋታቸው ልክ ለአላህ ብለን ነበር ወይ የጠላናቸውና ያራቅናቸው?! የሚለውም ጥርጣሬ ውስጥ ይከተናልና ቆም ማለት ተገቢ ነው።