Hintset: post #1368 — TG.ME

Forwarded fromMEMelkam Podcast
🎧 1ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3 ላይ ጌታ መልካም መሆኑን የቀመሱ ሁሉ፣ እኩዩን በመተው እግዚአብሔርን ወደ መምሰል የሚያደርሰውን ፈለግ እንዲከተሉ ሐዋርያው ምክሩን ይሰጣል።

👉 “መልካም ፖድካስት” ስያሜውን የወሰደው ከዚሁ ቅዱስ ቃል መነሻነት ነው። የፖድካስት ዝግጅቱ፣ ተስፋን የሚሰጥ፣ እምነት እና ዕውቀትን የሚጨምር እንዲሆን የተቃኘ ነው።

🌟 ታሪካዊ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጕዳዮች፣ ስለ እግዚአብሔር እና ሥራዎቹ፣ ስለ ትውልዱ እና ዘመኑ እንዲሁም የክርስትና ሕይወት መንገድን የሚመለከቱ ርእሰ ጕዳዮች የሚዳሰሱበት ሳምንታዊ ዝግጅት ነው።

🌟 እንግዶች ሆነው የሚቀርቡ ተጋባዦች፣ በየትኛውም የሙያ ዘርፍ እና የሕይወት ጐዳና ላይ ያሉ አማኞች ሲሆኑ፣ ክርስትናን በሕይወታቸው እንዴት እንደተረዱትና እንደሚኖሩት የሚያካፍሉበት፣ እግዚአብሔር በሕይወታቸው የሠራውን መልካሙን ሥራ የሚመሰክሩበት መድረክ ጭምር ነው።

🔖 የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎታችንን ይደግፉ፤ ለሌሎች ያጋሩ፤ የማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይከታተሉ።

https://linktr.ee/melkampodcast

እናመሰግናለን!🙏

#melkampodcast #new #comingsoon #መልካም #christianpodcast #discipleship
👏7👍2
June 29, 2026 1.9K 3