ይህን ታርክ ተጋበዙልኝ🥀 የዲኑ አቋሙ ጥሩ የሆነ አንድ ሐኪም እንዲት ሴት ያለባትን የስኳር በሸታ *… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

ይህን ታርክ ተጋበዙልኝ🥀

የዲኑ አቋሙ ጥሩ የሆነ አንድ ሐኪም እንዲት ሴት ያለባትን የስኳር በሸታ *

ለመመርመር ይሄዳል፡፡ ምርመራውን ከጨረሰ በኋላ ልጁን ወደ ቤት እንዲያደርሰው ላከችው:: በመንገድ ላይ እያሉ ሐኪሙ ልጁን ስለ ሶላትና ስለ ሌሎች ዲናዊ ጉዳዩች ጠየቀው ። ልጅም ሶላት ፋይዳ የሌለው ነገር እንደሆነ መለሰለት። ሀክሙም እሳት አትፈራም እንዴ ይለዋል። ልጅ ደግሞ የእሳት ሰዎች እጅግ በጣም ጥሩ ሰዎችናቸው፡፡, በማለት ይሳለቅበታል፡፡ በዚሁ ሐኪሙ ከመኪናው ወረደና ተለያዩ፡፡ ከዓመት በኋላ እንደገና ለዚያች ህመምተኛ ምርመራ ለማድረግ ብሎ ሄደ፡፡ ሲጨርስ ልጇ እንዲያደርሰው ጠየቀችው፡፡ ሐኪሙ አልፈለገም፡፡ እሷም ልጇ ዒሻ መስጂድ ስለሚሄድ ሰግዶ ወዲያውኑ እግረመንገዱን ይመለሳል፡፡› አለችው፡፡ በሁኔታው ተገርሞ ሊጠብቀው ወሰነ፡፡ በመንገድ ላይ እያለም የመለወጡን ምክንያት ጠየቀው፡፡ ልጅም የሆነውን ሁሉ እንዲህ በማለት ነገረው፡፡ በአንድ የጉዞ ድርጅት ውስጥ የሐጅ እና ዑምሪ ተጓዦች አስተናባሪ ሆኖ መሥራት የጅምራል እንደሆነና በአንድ ወቅት ከአንድ ቡድን ጋር ለዑምራ ሲሄድ በማረፊያ ክፍሉ ውስጥ ለብቻው ቀረ፡፡ ሐራም ነገርለመሥራት ባሰበ ቁጥር ዕድል ሊያገኝ አልቻለም፡፡ በመጨረሻም በሕይወቱ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕባን ለማየት ብሎ ሄደ፡፡ ዕለቱ የሸዕባን ወር የመጀመሪያው ቀን ጠዋት ሲሆን ከዕባ የሚታጠብበትና በሩም የሚከፈትበት ቀን ነበር፡፡ ብቻውን ቆሞ ሳለ ከኣሊ ሸይበህ ( የካዕባ ቁልፍ በእነሱ እጅ ነው ሚቀመጠው) የሆነ አንድ ሰው መጣና ‹ከዕባ ውስጥ ገብተህ መስገድ ትፈልጋለህን?” አለው፡፡ ይህን ዕድል ማን አግኝቶ፡፡ ወጣቱ ተደናግጦ በደመነፍስ ከዕባ ውስጥ ገባ፡፡ በመጨረሻም _ እንዲህ ይላል፡- እንደ አዲስ የምታጠብና አዲስ የተፈጠርኩ ነበር የመሰለኝ፡፡ ወደ ከዕባው ስገባ አመፀኛና በአላህ የካድኩ ስወጣ ደግሞ አማኝና አላህን አንድ አድርጌ አምላኪ ሆኜ ጌታዬ ሆይ! ተፀፅቻለሁ ጌታዬ ሆይ! ተፀፅቻለሁ እያልኩ ነበር፡፡›

እስቲ ልብ እንበል፡፡ አላህ ይህን ወጣት በየት በኩል እንደመጣበት! ለምን ቢባል እሱ ባሮቹን ስለሚወድ ነው፡፡ አንዳንዶች በፍጥነት፣ ሌሎች በምልክት ሌሎች ደግሞ በግድ ይገባቸዋል፡፡
ወደ ተውባ እንጣደፍ።
❤40😢14👍6🥰4⚡1🤗1
September 7, 2026 1.2K 4 13