ስማኝ ባል ተብየው!! ለሚስትህ ጥሩ ባል አለመሆን ዛሬ ላይ ትንሽ ደስታ ቢሰጥህም፣ ለነገው ግን ትልቅ ጸጸት… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

ስማኝ ባል ተብየው!! ለሚስትህ ጥሩ ባል አለመሆን ዛሬ ላይ ትንሽ ደስታ ቢሰጥህም፣ ለነገው ግን ትልቅ ጸጸት ሊያመጣብህ ይችላል።

አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል፦ «وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ»“ከእነርሱ ጋር በመልካም ሁኔታ ኑሩ።” (አል-ኒሳእ 4:19)

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ደግሞ፦ “ከእናንተ የተሻለው ለቤተሰቡ የተሻለ የሆነ ነው” ብለዋል

ስለዚህ ሚስትህን በፍቅር ያዝ አክብራት መብቷን ጠብቅ።የትዳር ህይወት የአላህ አደራ ነው አደራውንም በኃላፊነት ተሸከም።

ዛሬ የምታደርገው ለነገህ ይመዘገባል አላህን ፍራ ለባለቤትህም መልካም ሁን
❤38👏5
September 7, 2026 1.6K 33 15