የተግባር ፈተና ለምትወስዱ የአንስቴዥያ ባለሙያዎች በሙሉ
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በAnesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ በነሀሴ 2018 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና አልፋችሁ የተግባር ፈተና (OSCE) ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ፤ ፈተናው ጳጉሜ 03/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦
1 ሁሉም ተፈታኝ ጳጉሜ 02/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል ይኖርባችኋል።
2 በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ የብሄራዊ መታወቂያ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
3 ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
4 ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እያሳሰብን:-
- ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘውን ሰነድ በመክፈት የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያዎች መመልከት ይኖርባችኋል።
- ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
(ጤና ሚኒስቴር)
ለወቅታዊ ታማኝ የጤና መረጃዎች ⤵️
ቴሌግራም: https://t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0 ላይ ይከታተሉን::
ፌስቡክ: www.fb.com/tenachn
ዩትዩብ: youtube.com/@HIVN
ቲክቶክ: tiktok.com/@andu_tena
3September 4, 2026 2.2K