2.በፈተናው ወቅት የብሄራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print out ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
3.ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎችን፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
4.በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
5.በተጨማሪም ከስር የተያያዘውን የፈተና ሂደቱን የሚያሳይ ቪዲዎ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
6.ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ በታች የተያያዘውን ዚፕፋይል በመክፈት የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያ መመልከት ይኖርባችኋል።
ማሳሰቢያ፦
ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡










