Addis ababa Revenues Bureau: post #253 — TG.ME

በገዥው ተይዞ ስለሚከፈል ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም 15% ዊዝሆልድ ማድረግ የሚችሉት የፌደራል፣የክልልና የከተማ አስተዳደር የመንግስት መ/ቤቶችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም የተመረጡ የግል ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ከዚህ ውጭ ያሉ በ3 ተከታታይ ዓመታት 10 ሚሊዮንና በላይ ጠቅላላ ገቢ ያስመዘገቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች እና አክስዮን ማህበራት፣ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ህ/ስ/ማ፣ሽርክና ማህበር፣ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፣በጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም የኢትዮጵያ ማህበሮች ወዘተ…የምዝገባ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸው በግዥ ወቅት ከሚፈፅሙት ክፍያ ላይ 2% ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡በተመሳሳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢያቸው ከግምት ውስጥ ሳይገባ ዊዝሆልድ እንዲያደርጉ ግዴታ የተጣለባቸው፡ - ማንኛውም ባለኮኮብ ሆቴል ወይም ማንኛውም ሪዞርት - ከ1 እስከ 4 ደረጃ ያላቸው ስራ ተቋራጮች - ማንኛውም የሪልስቴት አልሚ - ምግብ አምራች ኢንዱስትሪዎች - በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግዥ የሚፈፅም ማንናውም ግለሰብ ግ/ከፋይ በምርት ገበያ በኩል ላደረገው ግብይት ብቻ - ሆስፒታሎችና በጤና ጥበቃ መስፈርት መሰረት ከፍተኛና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ክሊኒኮች - ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች - ከአምራች ኢንዱስትሪ ምርት በመረከብ የሚያከፋፍል ማንኛውም ግለሰብ ግ/ከፋይ

April 7, 2022 23.4K 34