የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣኔዎች /Rates የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሁለት የታክስ መጣኔዎች ይኖሩታል፡፡ እነሱም 15 ከመቶ መደበኛ መጣኔና ዜሮ ከመቶ መጣኔ የሚባሉት ናቸው፡፡ አስራአምስት በመቶ መጣኔ (መደበኛ መጣኔ) ▶️በተመዘገቡ ሰዎች የሚከናወን ታክስ የሚከፈልበት ግብይት፡- ✏️ታክስ የሚከፈልበት ግብይት” ማለት ከታክሰ ነፃ ከተደረገው አቅርቦት በስተቀር ታክስ የሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት የሚከናወን ማናቸውም የዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች አቅርቦት ነው፡፡ ✏️በተመዘገበ ሰው ስለሚከናወን ታክስ የሚከፈልበት ግብይት የተቀመጠው መመዘኛ ባልተመዘገቡ ሰዎች የሚከናወነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደማይመለከተው ያመለክታል፡ ✏️ሆኖም የተመዘገበ ሰው የንግድ ስራ ዕቃዎቹን ለግል ጥቅም ያዋላቸው ከሆነ የነዚህ ዕቃዎች አቅርቦት ታክስ ለሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ እንዳዋላቸው ይቆጠራል፡፡ ✏️ከታክሰ ነፃ ከተደረጉት በስተቀር በማናቸውም ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ▶️በዜሮ መጣኔ /0%/ ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች ☑️ለውጭ የገበያ የሚቀርቡ ዕቃዎችና አገልግሎቶች (Exports) ☑️ዓለም አቀፍ የዕቃ ወይም የመንደኞች የማጓጓዝ ተግባር፣ እንዲሁም በጉዞው አገልግሎት ላይ የሚውሉ የፍጆታ አቅርቦቶች፤ዓለም አቀፍ ጉዞው በአየር፣በባቡር፣በመርከብ፣በየብስ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡(እንደቅባት፣ዘይቶች እና ሌሎች አላቂ የቴክኒክ እቃዎች በቀጥታ ከጉዞው ጋር የተገናኙ መሆን አለባቸው ☑️ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወርቅ፣ ☑️አንድ የተመዘገበ ሰው ለሌላ የተመዘገበ ሰው አንድ ታክስ የሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ወይም ራሱን ችሎ የሚሰራ ታክስ የሚከፈልበት የንግድ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ክፍል /ሀብት/ ላልተወሰነ ጊዜ ይንቀሳቀሳል ተብሎ ለተቋቋመ ድርጅት ሲያስተላለፍ ☑️ዜሮ ከመቶ መጣኔ /0%/ ታክስ ይከፈልባቸዋል ሲባል ከእነዚህ ግብይቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ አይሰበሰብም ማለት ነው፡፡ ☑️አቅርቦቶቹ የሚቆጠሩት ታክስ እንደሚከፈልባቸው አቅርቦቶች (Taxable Suppiles) ሲሆን፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ለመመዝገብ በአጠቃላይ ዓመታዊ ሽያጭ ውስጥ ይታሰባሉ፡፡
Addis ababa Revenues Bureau: post #241 — TG.ME
March 30, 2022 16.1K 44