Addis ababa Revenues Bureau: post #240 — TG.ME

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች 🔹 ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ 🔹 የፋይናንስ አገልግሎቶች 🔹 ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት 🔹 በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች 🔹 የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች 🔹 በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች 🔹 ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች 🔹 ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ 🔹 ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች 🔹 መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች ) 🔹 የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ ) 🔹 የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም፡፡

March 24, 2022 12.6K 40