ክርስቲያን ነኝ️️️: post #299 — TG.ME

የዘማሪት ምስራች ህክምና በድል ተጠናቀቀ! "ከስድስት ወራት በፊት ከሀገር ስወጣ ምንም ተስፋ የለም ጥቂት ቀናት ብቻ ስጧት  ተብሎ በእግዚአብሔር ብቻ ላይ ባለ እምነት እና ተስፋ በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እህት እና ወንድሞቼ የገንዘብ የፀሎት እና የማበረታታት ሀይል በሞትና በህይወት መካከል ሆኜ ወደ ባንኮክ መጣሁ መሀሉ ብዙዙዙዙ ነው በሰፊ ምስክርነት ወደ እናንተ እመጣለሁ:: ሆኖም ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጬ በእግዚአብሐር አሸናፊነት 12 ከባባድ ኬሞዎችን ወስጄ ከሙሉ ፈውሴ ጋር ነገ አርብ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ወደ ሀገሬ ወደ ቤተሰቤ እንደገና በታላቅ ክብር እግዚአብሔር ላገለግለው በምድረ በዳዬ በሰጠኝ ዝማሬዎች እንደገና ልንፅናና በጉጉት እየጠበኩ ነው:: በዚህ ሁሉ ውስጥ እንደ ልጃችሁ እንደ እህታችሁ በእንባ የፀለያችሁልኝ ከጉድለታችሁ ለእኔ ህክምና የተቆረሳችሁ እግዚአብሔር ፀሎታችሁን ሰምቷል እና አመስግኑት እኔም የፈወሰኝን እርሱን ለእግዚአብሔር እጅ የሆናችሁለትን እናንተን እመሰግናለሁ ደግሞ ይህን አለፍኩ ስል በ12ኛው የመጨረሻው ኬሞዬን እየወሰድኩ ያመለጥኩት ጠላት በዚህ ላግኛት ብሎ ከባድ ይመሬት መንቀጥቀጥ ቢነሳም ከ20ኛው ፎቅ አንዳች ሳይነካኝ አምላኬ በባእድ ሀገር አተረፈኝ ስንቴ እድሜ እንደቀጠለልኝ እኮ ታዲያ በእንደገናው  በሁለተኛው ህይወቴ እስክሞት አገለግለዋለሁ   እንደገና ከሞትኩበት ቀስቅሶኛልና!" ስትል መልእክት አስቸላልፋለች። ዘማሪት የምስራች ስምኦን እግዚአብሔር ይመስገን!

April 3, 2025 305