ማንኛውም ሰው በአስተዳደር ኣካላት ያልተፈጠረ/ ያልተፈጠረ መብት ይዞ በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት መብት እንዲፈጠርለት የሚያቀርበው ክስ ከመጀመርያውኑ ፍ/ቤቶች በተፈጠረ ወይም በተቛረጠ መብት ላይ ኣከራክሮና ከህግና ማስረጃ ኣንፃር መርምሮ የመወሰን ስልጣን እንጂ ያልነበረ መብት የመፍጠርም ሆነ ያልተቛረጠ መብት በራሳቸው ተነሳሽነት የማቛረጥ ስልጣን ስለሌላቸው ክሱ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ዉድቅ ሊደረግ ይገባል፣ በሌላ በኩል የኣስተዳደር ኣካላት ዜጎች ለሚያቀርቡት የመብት ጥያቄ ህጉ በዘረጋው ስርዓትና ኣሰራር መሰረት ኣገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ግልፅ ነው፣ ስለሆነም ማንኛውም ሰው መጀመርያ ለኣስተዳደር ኣካሉ በህጉ መሰረት መብት እንዲፈጠርለት ጥያቄ ኣቅርቦ ከህግ ዉጭ ከተከለከለ ወይም ከህግ ዉጪ ተከልክያለው ብሎ ስያምን መብቱን ለማስከበር ፍ/ቤት ላይ የሚያቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለዉም ሊባል ኣይገባም፣ ምክንያቱም ፍ/ቤቶች የኣስተዳደር ኣካላት መብት ለመፍጠር የከለከሉበት ምክንያት ትክክል መሆን/ኣለመሆን ከህግ ኣኳያ መርምሮ የመወሰን ስልጣን ስላላቸው ነው፣ ሲጠቃለል መብት እንዲፈጠርልኝ ይወሰንልኝ ብሎ በቀጥታ ክስ ማቅረብ እና የኣስተዳደር ኣካሉ ከህግ ዉጭ መብት እንዳይፈጠርልኝ ከልክሎኛል ብሎ ክስ ማቅረብ ሁለት የተለያዩ የክስ ምክንያቶች ናቸው። #ያልታተመ_ውሳኔ_ሰመቁ_213046 #All_Business_Laws_and_Businesses_Free_Service https://t.me/GeezLaws
ማንኛውም ሰው በአስተዳደር ኣካላት ያልተፈጠረ/ ያልተፈጠረ መብት ይዞ በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት መብት… — Geez Laws Center ግእዝ የሕግ ማእከል — TG.ME
May 22, 2026 2.3K 40