የተእታ መመሪያው በጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ ታግዶአል:: ● በከሳሽ ጠበቆች እና በተከሳሽ ገንዘብ ሚ/ር መካከል በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባለው የተጨማሪ እሴት ታክስ መመሪያ ቁጥር 1104/2017 ክለሳ ክርክር ፍ/ቤቱ መመሪያው በመጀመሪያ ክሱን ላቀረብን 7ቱ ጠበቆች ሳይፈጸም ታግዶ እንዲቆይ ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ትእዛዝ መስጠቱ ይታወሳል:: ● ከዚህ ቀን በኋላ የተለያየ ቁጥር ያላቸው አድራሻቸውን በፌደራልና በክልል ያደረጉ ጠበቆች በተለያዩ 30 በላይ መዝገቦች ክስ ያቀረቡ እነዚህን ጠበቆች አስመልክቶ ግን እግድ እንዳልተሰጠም ይታወቃል:: ● በዚህ የእግድ ክልከላ ብይኑ ቅር የተሰኙ ጠበቆች ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ እንዳቀረቡ እና እያቀረቡ እንደሆነም ይታወቃል:: ● ከእነዚህ የይግባኝ መዝገቦች መካከል ቀድሞ በተከፈተው መዝገብ ላይ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰሞኑን አቤቱታውን ሰምቶ ያስቀርባል በማለት ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ የመመሪያ ቁ.1104/2017 አፈጻጸም ይግባኝ ባይን አስመልክቶ ታግዶ እንዲቆይ በማለት ዛሬ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል:: @EthiopianLaw [email protected] #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws
12
1May 15, 2026 1.7K 6