በሕፃን ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍቺ ንብረት ክፍፍል ጊዜ የማን ይሆናል? • በትዳር ፍቺ… — Geez Laws Center ግእዝ የሕግ ማእከል — TG.ME

በሕፃን ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍቺ ንብረት ክፍፍል ጊዜ የማን ይሆናል? • በትዳር ፍቺ ምክንያት በሚደረግ የንብረት ክፍፍል መመለስ ካለባቸው አሻሚ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከጋራ ንብረታቸው የተገዛ የማይንቀሳቀስ ንብረት በህፃን ስም ያስመዘገቡ ባልና ሚስት በፍቺ ሰዓት በዚሁ ንብረት ክፍፍል ላይ ጭቅጭቅ መነሳቱ አይቀርም:: • ከዚህ በፊት ሕፃኑ ከራሱ ሀብት ወጪ አድርጎ የገዛው ወይም ያፈራው ንብረት መሆኑን ካላስረዳ የባልና ምስት ሀብት ነው ተብሎ ይወሰናል ነበር::ይሁን እንጂ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አድስ ውሳኔ ሰቷል:: በዚህ ጉዳዩ ሕጉ ምን ይላል? • አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በህፃኑ በሕጋዊ መንገድ የተፈራ ንብረት ስለመሆኑ ግምት ሊወሰድ ይገባል፡፡ • ህፃኑ ንብረቱን ከራሱ የሃብት ምንጭ ወጪ አድርጎ ስለመግዛቱ አላስረዳም በሚል ምክንያት ንብረቱን ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት እንጂ የህፃኑ አይደለም በማለት መወሰን አግባብነት የለውም፡፡ • ባልና ሚስቱ ንብረቱን በራሳቸው ፈቃድ ከጋራ ንብረታቸው ወጪ በማድረግ አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም የገዙ ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ህፃናትን የሚመለከቱ ጉዳዮች የህፃናትን ደህንነትና ጥቅም በቀደምትነት ታሳቢ ማድረግ እና ለህፃኑ ጥቅም ተብሎ እንደተገዛ (እንደተፈራ) ንብረት ተደርጎ ሊወሰን የሚገባው ነው ተብሎ ተወስኗል። • ሰበር መ.ቁ 41/2010 [email protected] #Free_Services +251948449999 #All_Business_Laws & Businesses https://t.me/GeezLaws

TelegramGeez Laws Center ግእዝ የሕግ ማእከልwww.geezlaw.com | +251948449999 [email protected] #Free_Services #All_Business_Laws & Businesses
May 15, 2026 1.6K 14