ድምፅ ብቻ እንሁን!
ትዝ ይላችኋል ወዳጆችዬ የመጥምቁ ዮሀንስ ህይወት
ገና ሳይወለድ ከዘመናት በፊት ነብዪ ኢሳያስ የተነበየት ትንቢቱ እንደዚህ ከምቾት፣ ራስን ከማስደት ፈፅሞ የራቀ ኑሮ ምድረበዳ ምግቡ አንበጣ ይልቅ የሰማይን ፍቃድ በምድር መጮሂዬ የሰዎችን ትኩርት ከእግዜሩ መመለስ ይሄ ነው ትንቢቱ!
አባቱ ካህን ሽማግሌ እናቱም አሮጊት በጌታን ትዕዛዝ ያለ ነቀፋ የሚሄዱ ፃድቃን
ታድያ አንድ ቀን ካህኑ በተራው ወደ ቤተመቅድስ ለማጠን ሲገባ ቅዱሱ የጌታ መልዐክ ምስራች ይዞ ከተፍ የመጣው መልክት ልጅ ትወልዳላች ታላቅ ሰው ይሆናል ይህማ እልልልታ በእርጅና የተገኛ ተድላ ግና ይሄኛው እንደተለመዱት ተጠባቂ ልጆች ፈፅሞ አይደለም
እርሱ አገልጋይ ነው
የጌታውን ፍቃድ
መንገድ ጠራጊም ነው ለሚመጣው ንጉስ ፤ልብን ይመልሳል ወደ አምላክ ማርኮ፤ ድምፅ ብቻ ሆኖ ዋናውን ይገልጣል
እንደተባለልት አድጎም አገልጋይ ነው ነፍሳት የሚማርክ ወደ እግዚአብሔር ጉያ ሰውን የሚጠራ ወደ ንሰሀ ጥምቀት
ይህን ያዩ አይሁድ ወደ እርሱ ቀረበው
ይህን ምታደርገው በየትኛው ስልጣን
ኧረ እስኪ ንገረን
እንደው ስንጠረጥር ኤልያስ መሰልከን ወይስ ክርስቶስ ነህ እንደውም ኢሳያስ ነህ ብለው ሲሞግቱት የመጥምቁ ምላሽ ፐ እንዴት አወቃችሁ እኔማ ይገርማችኋል ብሎ አልሰበትም ራስ ተኮሩ ላይ እኔማ የሚጮህ ድምፅ ነኝ!
ሚመጣ አካል አለ ከእኔ ለጥቆ
መንገድ ጠራጊው ነኝ ።
እንደው ካላችሁማ አንተ ማነህ ??
በውሀ አጥማቂ የንጉሱ ባሪያ ፤ጫማው ልሸከም ከቶ ማይገባ፤ እኔ ላንስ ሚስፈልግ እሱ ሊልቅ ሚገባ የእርሱ አገልጋይ ነኝ!
ይበቃል አትክረሙ እኔ ላይ እሱን ተመልከቱና ባይሆን ንሰሀ ግቡ ለሚመጣው ንጉስ ልባችሁን ክፈቱ ነበረ ምላሹ!
ለራሱም አልኖረ ምቾት አልፈለገ ለእውነት ሲሞገት በሞቱም ጌታን አከበረ ጌታም መሰከረ ስለ አኗኗሩ
ከሴት ከተወለዱት የሚመስለው የለም!
ላኪውን ያስደሰተ ህይወት
እኛም ወዳጆቼ ለዚህ ተጠርተናል
ንጉሱ ሊመጣ በደጅ አለሁ ይላል
የጌታን መንገድ ለመጮህ መጥተናል መንገድን ለመጥረግ
ብዙዎችን ወደ ጌታ ለመመለስ
ከእኛ ኋላ የሚመጣው የላቀ እንደሆነ
እኛ ግን ያነስን እሱን ለማሳየት ለዚህ ተጠርተናል
እናማ ራስን ለማሳየት ትኩረትን ለመሳብ ይቅር አንጋጋጥ ይልቅ ከኛ የላቀ አለ የሚታይ የሚሰማ የሚያደን
እሱን ብቻ እንግለጥ
እኛ ድምፅ ብቻ እንሁን!
🎼ድምፅ ነኝ እኔ የምጮህልህ
ማለት ያሰብከውን ማስተጋባልህ
ይሄው ነው ስራዬ መላክ ስትልከኝ
ልጅህን ማሳየት አድርጊ እንዳልከኝ🎼
ተባረኩልኝ
በ እህት ቃል







