ኦሪት ዘፍጥረት 👉ምዕራፍ 10 ላይ ከቁጥር1-31 የኖኀ ልጆች የሴም የካም እና የያፌት ትውልድን ይዘረዝራል… — ፍኖተ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት ቤተመጻሕፍት ክፍል — TG.ME

ኦሪት ዘፍጥረት 👉ምዕራፍ 10 ላይ ከቁጥር1-31 የኖኀ ልጆች የሴም የካም እና የያፌት ትውልድን ይዘረዝራል ከዚያም 👉ከቁጥር 32 የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።አሕዛብም ከጥፋት ውሃ በኋላ በምድር ላይ ከነዚህ ተከፋፈሉ። በቀጣዩ ምዕራፍ 11 ላይ 1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። 2 ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። 3 እርስ በርሳቸውም፡— ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው። 4 እንዲህም፡— ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው፡ አሉ። 5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6 እግዚአብሔርም አለ፡— እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። 7 ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። 8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። 9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። 10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ። 👉ከቁጥር 10-32 የሴምን ትውልድ ይዘረዝራል

June 5, 2025 218