• ይህን ችግር ለመቅረፍ የተነሡት የዘመኑ ፓትርያርክ ከሀቢብ ጊዮርጊስና ከሌሎች ሁለት ምእመናን ጋር በመሆን ሐዋሪያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ሀቢብ በውጪ የሚገኙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶችን የሚሰበስብበትን ዘዴዎች መመልከት የቻለው፡፡ ወዲያውኑ ከጉዞው መልስም ህጻናትና ወጣቶች ተሰብስበው የሚመሩባቸውን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማደራጀትና የሚመጥናቸውን ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ መንፈሳዊ መዝሙራትንም ለማዘጋጀት አቅዶ ሥራውን ጀመረ፡፡ በዚህ ሥራውም በሌላ እምነት ተማርከው የነበሩትን መመለስ ችሏል፡፡
ሀቢብ ጊዮርጊስ #ጸሐፊነትን፣ #አስተዳዳሪነትን እና #ሰባኪነትን በእኩል ደረጃ አሳክቶ መያዝ የቻለ ሰው ነው፡፡ በአጠቃላይ #ሠላሳ_መጽሐፍትን አዘጋጅቷል፡፡ በመጨረሻ ዕድሜው ሲገፋ #ጤናውም_እየታወከ_መጣ፤ ቤቱም በደቀ መዛሙርቱ መሞላት ጀመረ፡፡ ለእርሱም የነበራቸውን ፍቅር ለመግለጽ መኝታን ከበው አብረውት ጸሎት በማድረግ ራሱ የደረሳቸውን #መዝሙራትም_ይዘምሩለት ነበር፡፡
በመጨረሻ ሀቢብ ጊዮርጊስ ነሐሴ 15 ቀን 1943 ዓ.ም (በ75 ዓመቱ) አረፈ፡፡ ዜና እረፍቱም በሀገረ ግብፅ ከዳር እስከ ዳር ተሰማ፡፡ ቀብሩም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት መስከረም 17 ቀን 1944 ዓ.ም ተፈጸመ፡
ምንጭ፡-ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ እና ሥራዎቹ፣ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958




















