የተከሳሽ ንብረት ከሆነው ስልክ ውስጥ የተገኘው ቪዲዮ ላይ የሚታየው የእገታና የማሰቃየት ወንጀል የተፈጸመው… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🚨🇪🇬 የተከሳሽ ንብረት ከሆነው ስልክ ውስጥ የተገኘው ቪዲዮ ላይ የሚታየው የእገታና የማሰቃየት ወንጀል የተፈጸመው በ2021 ነው ። በዚህ ቪዲዮ ላይ አንድ የታገተ ሰው ሲደበደብ እና ሲሰቃይ ፡ እንዲሁም እርቃኑን በማድረግ ክብሩን የሚነኩ እና አዋራጅ ድርጊቶችን እንዲፈጽም ሲያስገድዱት ይታያል ።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለም ከአሁን በኋላ ይህንን የተፈጸመበትን እገታና ድብደባ እንዲሁም ከዚህ በፊት የሚያውቃቸውን ሚስጥሮች ለፖሊስ ቢናገር ፡ ይህንን ራቁቱን ሆኖ የሚታይበትን ቪዲዮ በሶሻል ሚዲያ ፖስት እንደሚያደርጉት ሲያስጠነቅቁት ይሰማል ።

ይህንን ጉዳይ እዚህ ላይ ፖዝ አድርገን አሁን ስለሳራ ካሊፋ እናውራ ።
........
ሳራ ከሊፋ ትባላለች ፡ ግብጻዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ፡ እና የተለያዩ ካምፓኒዎችን የምታስተዳድር ሴት ናት ።

ሳራ 2.5 ሚሊየን ፎሎወር ባለው የኢንስታግራም አካውንቷ በየጊዜው በምትለቀው ፎቶና ቪዲዮ ፡ ቅንጦት ማለት ፡ ሀብት ማለት ፡ ምን ማለት እንደሆነ የሚያሳዩ ናቸው ።

...በቻኔል ጉቺ እና ቪቶን ውድ አልባሳት ዘንጣ
ውድ ዋጋ በሚከፈልባቸው የፓሪስ ሬስቶራንቶች ሺህ ዶላር የሚያወጣ በሻማና በሻምፓኝ የታጀበ ራት እየተመገበች ፡ ቀን በሉቭር ሙዚየም ስለተመለከተችው የሞናሊዛ ስእል የምትናገር ።
......
በማያሚ ቢች ላይ እየተንሳፈፈች ባለች የቅንጦት ጀልባ በረንዳ ላይ ነጭ የሀር ጋዋን ለብሳ ፡ በትልቅ ስስ ብርጭቆ ብርማ ቀለም ያለው አንጸባራቂ ነገር እየጠጣች ስለቀን ውሎዋ የምትተርክ ሴት ናት ።
.....
ይህች ዝነኛ እና ሀብታም ሴት በሀገሯ ግብጽ ውስጥም ፡ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የስፖርት መኪናዋን እያጓራች በካይሮ ጎዳናዎች ላይ የምትታይ ።
እኔ ነኝ ባለው ቅንጡ ህይወቷ የምትታወቅ ፡ በዋና ከተማዋ ምርጥ ምርጥ በሚባሉ የግል ቪላዎቿ የምትኖር ፡ ሀብት ብቻ ሳይሆን ግብጽን ከዳር እስከዳር ያዳረሰ ታላቅ ዝና ያላት ታዋቂ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ፡ የቀድሞ ሞዴልና ኢንቨስተር ናት ።
...
ሆኖም
......
በኤፕሪል 2025 ባላት ሀብትና ዝና እንዲሁም ከተለያዩ ባለስልጣናት ጋር ባላት ቅርርብ የምትታወቀው ሳራ ካሊፋ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ተነግሯት በፖሊስ ተወሰደች
......

ጣቢያ እንደደረሱም ታዋቂዋ ዝነኛዋና ሚሊየነሯ ሳራ ከሊፋ አደንዛዥ ዕፅ በማምረት በማከፋፈል እና የወንጀል ቡድኖችን በመምራት እንደምትፈልግ ተነግሯት ክስ ተመሰረተባት ።
......

ፖሊስ ሳራን በቁጥጥር ስር አውሎ በግብጽ ውስጥ ያሏትን ዘመናዊ ቪላዎች መፈተሽ ጀመረ ።
በዚህ ፍተሻ ወቅትም ፡ 750 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እፅ እና የእጽ ማቀነባበሪያ ላቦራቶሪ አገኘ ። ይህ ብቻ አይደለም ሳራ ከሌሎች ተባባሪዎቿ ጋር በመሆን የወንጀልና የእገታ ድርጊት እንደምትፈፅም የሚያስረዱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ፡ ድርጊቱን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ቪዲዮዎችን ከራሷ ስልክ ላይ አግኝቷል ።
ከነዚህ መሀከል ቅድም ከላይ በመግቢያችን ላይ ያነሳነው ሰው ጉዳይ ነው ።
.....
ይህ የእገታና ድብደባ ወንጀል የተፈጸመበት ሰው የቀድሞ የሳራ ሾፌር የነበረ ሲሆን ፡ ከፖሊስ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ጥርጣሬ ወደሳራ ቪላ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ
ስለትን ያካተተ አደገኛ ድብደባና እንግልት እና ሌሎች አዋራጅ ነገሮች እንደተፈጸሙበት ፡ ራቁቱን አድርገው ቪዲዮ ከቀረጹት በኋላ ፡ ከንግዲህ አንዳች ሚስጥር ቢያወጣ ቪዲዮውን በሶሻል ሚዲያ ፖስት እንደሚያደርጉት አስጠንቅቀው ስለለቀቁት ከማፍያው ቡድን ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት በመስጋት ፡ በነሳራ ከሊፋ ወንጀል እንደተፈጸመበት ሳይናገር ለአመታት ቆይቷል
...
ፖሊስ ይህንን ቪዲዮ ከሳራ ስልክ ላይ ካገኘ በኋላ ግን አደንዛዥ እፅ ከማምረትና ማሰራጨት ወንጀል በተጨማሪ የእገታና ውንብድና ተግባር መፈጸም የሚል ሌላ ተጨማሪ ክስ ተመስርቶባት ላለፉት 14 ወራት በእስር ቤት ሆና ክሷን ስትከታተል ቆይታ ነበር ።
...........
በግብጽና በዱባይ ራሱ ግዙፍ ቪላዎች ያሏት ፡ ከአሜሪካና እስከ አውሮፓ ፡ ከኤዥያ እስከ አፍሪካ ፡ የቅንጦት ኑሮዋን በኢንስታግራም ፖስት እያረገች ብዙዎች እሷን መሆን እንዲመኙ ያደረገችው ፡
በአደንዛዥ እጽ የብዙዎችን ህይወት ያመሰቃቀለች ፡ ሚስጥራዊ የወንጀል ቡድን መሪ ትሆናለች ብሎ ማንም አስቦ አያውቅም ነበርና በዚህ ወንጀል ተጠርጥራ ስትያዝ በተለይ ለግብጻውያን አስደንጋጭ ዜና ነበር ።
.......
በዚህ መልኩ ላይዋን አሳምራ ለአመታት የኖረችው ሳራ ካሊፋ መጥፎ ስራዋ ጊዜው ደርሶ ተገለጠና ለወራት ሲካሄድ የቆየው የክስ ሂደት ተጠናቆ ትናንት 11 ከሚሆኑ የቡድን አጋሮቿ ጋር በግብጽ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባታል
.....
አሁን ያ ሁሉ የቅንጦት ህይወት ተረት ሆኗል ። ሚሊዮኖች የፈሰሰባቸው ቪላዎቿን ከንግዲህ አትኖርባቸውም ። በወንጀል እና በሰው dm የተገኘው ሀብት ፡ ውድ አልባሳቶቿ ፡ አስር ሺህ ዶላሮችን የሚያወጡ ሽቶዎች ከንግዲህ የሉም ። አደለም እነዚህ ትርፍ ነገሮች ከንግዲህ በነጻ የሚገኘውንም አየር ትቀማለች ።
የ39 አመቷ ሳራ ካሊፋ በድብቅ ለሰራችው የአመታት ወንጀል ፡ በግልፅ ሊከፈላት ቀናት ብቻ ይቀራሉ ።

~ ዋሲሁን ተሰፋዬ እንደፃፈው ✍️


ቴሌግራም፦
            📌t.me/Brics4ethiopia
❤9
September 6, 2026 357 2