የየመን ሁቲዎች በዛሬው እለት በሳኡዲ አረቢያ ላይ ከባድ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ሲፈፅሙ ነው የዋሉት።… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🎁 የየመን ሁቲዎች በዛሬው እለት በሳኡዲ አረቢያ ላይ ከባድ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ሲፈፅሙ ነው የዋሉት።
በዚህም በርካታ ከተሞች የጥቃቱ ሰለባ ሲሆን የነዳጅ ተቋማትና ተሽከርካሪዎችም ነደዋል። ከ 73 በላይ ሳኡዲያዊያንም የጥቃቱ ሰለባ በመሆን ጉዳት አስተናግደዋል።
የአራምኮ የነዳጅ ጣቢያዎች የተመቱ ሲሆን አብሀ ፣ ጂዛን ፣ ነጂራን እና ኸሚስ ሙሻኢት ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ከተሞች ናቸው።
ሳኡዲ አረቢያ ከሁቲዎች ጋር የምታደርገው ጦርነት ሁሌም ዋጋ እንዳስከፈላት ነው።
ይሄንን ጦርነት ተደራድራ ካላስቆመች በስተቀርም ሳኡዲ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ውድመት ይደርሶባታል።
ሳኡዲ ለጥቃቱ አፀፋውን እንደምትመልስ አሳውቃለች።


ቴሌግራም፦
            📌t.me/Brics4ethiopia
September 8, 2026 244