🗺️🌍የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።🌎🌍
በቶጎ አቅራቢነት እና በአፍሪካ ህብረት ደጋፊነት የቀረበውን ይህንን የውሳኔ ሀሳብ በ164 ሀገራት ድጋፍ ሲጸድቅ ፣አሜሪካ ብቸኛ ተቃዋሚ ሀገር ሆና ተመዝግባለች። 6 ሀገራት ደግሞ በዉሳኔው ላይ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
እስካሁን ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው የመርኬተር ካርታ ከምድር ወገብ ርቀው የሚገኙ ሀገራትን አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ የአህጉራትን እውነተኛ መጠን ያዛባ ነበር።
በነባሩ ካርታ ላይ ግሪንላንድ እና አፍሪካ እኩል ተደርገው ቢሳሉም፣ በእውነታው ግን አፍሪካ ከግሪንላንድ በ14 እጥፍ ያህል መብለጧ በጉባኤው ላይ በማሳያነት ቀርቧል።
ጉዳዩን በማነሳሳት ለጉባኤው እንዲቀርብ ያደረገችው የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ዱሴ ውሳኔውን "ታሪካዊ" ሲሉ አወድሰዉታል። ጉዳዩ «የካርታ ስራ ብቻ ሳይሆን የፍትህ፣ የክብር እና የእኩልነት» ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
አዲሱ የውሳኔ ሀሳብ ነባሩን ካርታ ሙሉ በሙሉ የሚያግድ ባይሆንም፣ ትምህርት ቤቶች፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በ2018 የተሰራውን እና ለችግሩ ምላሽ ይሰጣል የተባለውን የ"ኢኳል ኤርዝ" ካርታ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።
የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ ነባሩ የተዛባ ካርታ በትምህርት፣ በሚዲያ እና በፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር መቆየቱን በመግለፅ አዲሱን ውሳኔ ደግፎታል።
📷 ካርታውን ለማያት ከፈለጉ ይኸው ፦👇👇
https://t.me/Brics4ethiopia/6024?single

Telegram
BRICS 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
🗺️🌍የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።🌎🌍
በቶጎ አቅራቢነት እና በአፍሪካ ህብረት ደጋፊነት የቀረበውን ይህንን የውሳኔ ሀሳብ በ164 ሀገራት ድጋፍ ሲጸድቅ ፣አሜሪካ ብቸኛ ተቃዋሚ ሀገር ሆና ተመዝግባለች። 6 ሀገራት ደግሞ በዉሳኔው ላይ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
እስካሁን…
5September 5, 2026 479