መብትህ ነው። በእኔ በኩል ያን መብትህን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ አከብራለሁ። ነገር ግን በፖለቲካ “እርድና” ህዝብን ለማደናገር መሞከር ተገቢ አይደለም። ትክክለኛውን አቋምህን በግልጽ ይዘኸው ውጣና እንወያይበት፣
እንከራከርበት። በአሁኑ ወቅት ሀገራችንና ህዝባችን የተጋረጠባቸውን የህልውና አደጋ እንኳንስ በሸፍጥ፣
በሀቅም ታግለን ልንሻገረው ከባድ ነው።
ስለሆነም ከአላስፈላጊ የፖለቲካ ጨዋታ ሁላችንም ብንወጣና
አቅማችን በፈቀደ መጠን ህዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት ለመታደግ በቅንነትና በሀቅ ብንታገል የተሻለ ነው
እላለሁ። አቶ ጀዋር፣ አሁንም ያለ አግባብ ተፈርጃለሁ ብለህ የምታምን ከሆነ እኔና አንተ በርቀት ጽሁፍ እየተወራወርን
መቀጠል ያለብን አይመስለኝም። በፈለግኸው መገናኛ ብዙሃን ቀርበን በጨዋነት እንድንወያይ ወይም
እንድንከራከር አሁንም ግብዣዬን በድጋሜ አቀርባለሁ።
ከታላቅ አክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው።
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
1September 4, 2026 475 1