📸 #ርዕሰ_አንቀጽ: የመድፍ ቀለብ መሆን ይብቃ!
የአንድ አገር መንግሥት ወይም ባለሥልጣናት ዜጎች ለሚያምኑበት ዓላማ እንዲታገሉ ማሳመን አቅቷቸው፣ ለማያምኑበት ጦርነት በኃይል ማገድ ሲጀምሩ፣ ያ ክስተት በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ እና የሞራል ውድቀት መኖሩን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ዜጎችን ለወታደራዊ ተግባር በኃይል የመመልመል አደገኛ አካሄድ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ዳግም ከተመለሰ ሰንበትበት ብሏል።
ወጣቶች በሚጓዙበት ወይም በሚሠሩበት ወቅት ይያዛሉ፤ አርሶ አደሮች ወደ ወታደራዊ ስልጠና እንዲገቡ ይገደዳሉ፤ ቤተሰቦች የታሰሩ ዘመዶቻቸውን ለማስፈታት ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ፤ ለአካባቢ ባለስልጣናት የሰው ቁጥር ኮታ ይሰጣቸዋል፤ ወጣቶች ወደ ወታደራዊ ካምፖች ሲያመሩ የቤተሰብ መኖሪያና ህይወት ይናጋል።
ይህ አገራዊ ህዳሴ ሳይሆን አገራዊ ውድቀት ነው!
https://addisstandard.com/Amharic/?p=14012

Addis standard
የመድፍ ቀለብ መሆን ይብቃ! - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28/ 2018 ዓ.ም:- የአንድ አገር መንግሥት ወይም ባለሥልጣናት ዜጎች ለሚያምኑበት ዓላማ እንዲታገሉ ማሳመን አቅቷቸው፣ ለማያምኑበት ጦርነት በኃይል ማገድ ሲጀምሩ፣ ያ ክስተት በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ እና የሞራል ውድቀት መኖሩን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ዜጎችን ለወታደራዊ ተግባር በኃይል የመመልመል አደገኛ አካሄድ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ዳግም ከተመለሰ ሰንበትበት…
4September 4, 2026 351 1