ስንቱን እናስተምር ? አረ ክርስቲያን ወገኖች ቢያንስ ትንሽ ተማሩ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደምታውቁት ኢየሱስ… — FACE THE TRUTH — TG.ME

🔘ስንቱን እናስተምር ? አረ ክርስቲያን ወገኖች  ቢያንስ  ትንሽ ተማሩ

መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደምታውቁት ኢየሱስ የተሰቀለበት ቀን ላይ ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ድረስ ምድር ጨለማ ሆኗል ይላል። ከላይ ልጁ የከፈለተው ማቴዎስ ወንጌል ላይ እንዲሁም ሉቃስ 23:44 ላይም ይናገራል። አታስቡ ይህ መረጃ የሌለው ቀደዳ ነው። ይህ ክርስቲያን ልጅ ለውይይት ሲመጣ አጠሬራ የሚሰጡ አስተማሪዎቹ lunar eclipse የፀሀይ ግርዶሽ መስሏቸው ለልጁ የፀሀይ ግርዶሽ ነው ብለውት ይኸው ኢየሱስ ሲሰቀል ቀኑ ጨለመ ለሚለው መረጃ ብሎ በlunar eclipse ምክንያት ነው ቀኑ የጨለመው እያለ ነው 😭። lunar eclipseኮ የፀሀይ ሳይሆን የጨረቃ ግርዶሽ ማለት ነው። የጨረቃ ግርዶሽ ከቀኑ ብርሃን ጋ ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ጨረቃ አይደለችምኮ ቀኑን ብርሃን የምታደርገው ፀሀይ ናት 😂

የጨረቃ ግርዶሽ ከላይ በፎቶ እንደምታዩት ምድር በፀሀይ እና ጨረቃ መሀል ገብታ ወደ ጨረቃ የሚሄደውን ብርሃን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ስትጋርደው  ያኔ ጨረቃ ስለተጋረደች የጨረቃ ግርዶሽ ይፈጠራል።ምድር ግን የፀሀይ ብርሃን እየደረሳት ነው ስለዚህ አይጨልምም። ፀሀይ ብትጋረድ ነበር የሚጨልመው።

ክርስቲያን መምህራን እባካችሁ ሚስኪን ተማሪዎቻችሁን የማይሆን አጠሬራ ሰጥታችሁ መለማመጃ አታርጓቸው። እናንተም ራሳችሁን በዚህ ልክ አታዋርዱ !

✍️ Abdulkerim

https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
😁172👍89❤20🔥14😱3😇2
September 3, 2026 3.6K 23