የሙስሊም ሚዲያዎችን አንድ ልንላቸው ይገባል !
🔘 አንዳንድ የሙስሊም ሚዲያዎች በእስልምና የማይፈቀደውን ድብድብ ሙስሊሙ ህዝብ መሀል በማጋጋል ስፖርቱን ወደ ኃይማኖት በመቀየር ሌላ አይነት ነገር እያስመሰሉት ነው። ይህ የምታዩት ማስተር ሀሰን ይባላል ። በጣም ጠንካራ በቻይና እንዲሁም ሌሎችም ሀገራት ሄዶ በተለያዩ ስፖርቶች በመሳተፍ አሸንፏል። ይህ እንደ ግሉ ስናየው መልካም ሆኖ ሳለ ከፈለገ ራሱን ችሎ ለመወዳደር መግባት ሲገባው ነገሩን የኃይማኖት አድርጎ በማሰብ እና በዛ እልህ ሆኖ ለመግባት ማሰብ ጭራሽ ደግሞ ይህን በአደባባይ መናገር ትክክል አይደለም ።
🔘በነገራችን ላይ በውድድሩ ሙስሊም አሸናፊዎች ነበሩ ለምሳሌ ረቢቅ ሳኒ በዝረራ ሲያሸንፍ በተከታታይ 2ኛ ጊዜ ነው። ዘሀራም አሸንፋለች። ከጆኒ ቡድኖች ውስጥ አንዱ እድሪስ ነው እሱም አሸንፏል። ነገር ግን ግሎ የተነሳው የሴዶ መሸነፍ ነው። ሴዶ ስላልሰራ ተሸነፈ እንጂ በኃይማኖት አይደለም ። ጆኒ ራሱ አስተማሪው ሙስሊም ነው ። ኡመር ጀማል ነው ብለን ብንጮህ ሊሰሙን አይደለም ። በአለም ደረጃ UFC ላይ ራሱ የነገሱት ሙስሊሞች ናቸው። የሙስሊም ሚዲያዎች ግን ህዝቡን አጉል ነገር ውስጥ እየከተቱት ነው።
በነገራችን ላይ በኢስላም የቦክስ ውድድር አይቻልም ይህን ረስቼ አይደለም ግን መጀመሪያ ህዝቡ ላይ ያለው እየተዘዋወረ ያለው የተዛባ ነገር ላጥራ ብዬ ነው ስተነትንላችሁ የቆየሁት። ከኢስላም አንፃር ያለውን ነገር እነግራችኋለሁ።
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------



