በኅብረት ለሀገር የቆመው ሠራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
ማንኛውም ታሪካዊ ክስተት የአንድን ኃይል እውነተኛ ማንነት የሚፈትሽበት የራሱ መመዘኛ አለው በከባድ የተፈጥሮ መልክዓ-ምድርና በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ውስጥም ቢሆን ሉዓላዊነትን ሳያስደፍር ሕዝባዊ አደራን በታማኝነት ተሸክሞ ለዘመናት የጸናው የመከላከያ ሠራዊት ዛሬም በዕለተ ኅብር ለሀገረ መንግሥቱ ህልውና አስተማማኝ ዋስትና ሆኖ ይገኛል።
የተዋጊነት ሕይወት እያንዳንዱ ቅጽበት ታላቅ መሥዋዕትነትንና ራስን አሳልፎ መስጠትን የሚጠይቅ በመሆኑ በአስተማማኝ ምሽጎች ላይ የሚገኙ ጀግኖች የሀገርን አንድነት የሚፈታተኑ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቆራጥነትና በወታደራዊ ጥበብ በመመከት የገቡትን ታላቅ ቃል ኪዳን በተግባር በማረጋገጥ ላይ ናቸው።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአዲሱን ዘመን መባቻ ለመቀበል በከፍተኛ የደስታ ስሜት ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ሠራዊቱ ግን ለአፍታም ሳይዘናጋና ንቃተ-ሕሊናውን ሳይቀንስ ጥበቃውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ወታደር ማለት በራሱ የኅብረትና የአንድነት ሕያው ዓምድ ማለት ሲሆን ለረጅም ዘመናት ቃሉን ሳይቀይር በተሰጠው የግዳጅ ስምሪት ቀጠና ሁሉ ሳይነቃነቅ የሚገኝ ለአላማው ታማኝና ፈታኝ ሁኔታዎችን ሁሉ በልዩ ጥንካሬ በማለፍ ለትውልድ አርአያ የሚሆን መሠረት እሱ በመሆኑ ነው።
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ የተለያዩ ቋንቋዎችና ባህሎች ባለቤቶች በአንድ ዓላማ ሥር ሲሰለፉ የማሸነፋቸውና ሁልጊዜም በድል የመውጣታቸው እውነተኛ ምስጢር በአጋጣሚ ወይም በተአምር የተገኘ አይደለም ሁሌም በሁለንተናዊ ድጋፍ ከጎናቸው የማይለየውና እንደ ጽኑ አለት በስተጀርባቸው የቆመው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።
ይህ እምነትና ጽናት ከድንበር አልፎ የአፍሪካውያን ኩራት የሆነውን ታላቁን የታሪክ ገድል ጠብቆ ያቆየ የሀገርን ክብር ሊደፍሩ የመጡ የውጭ ወራሪዎችንና የውስጥ ተላላኪዎችን በተባበረ ወታደራዊ ክንዱ ጠራርጎ ያስወገደ የነጻነት ምልክት ነው።
ዛሬ ጷጉሜ 04 የኅብር ቀን ሲከበር ሠራዊቱ የሕዝቡን ደኅንነት ከራሱ ሕይወት አስቀድሞ ሁሉንም ጸረ-ሰላም ኃይሎች በብቃት በመመከት የሀገርን ቀጣይነት እያረጋገጠ አዲሱን ዓመት ለማክበር የዛሬን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣትና ነገን በበለጠ ዝግጁነት ለመቀበል ሠራዊቱ የገባው ቃል ኪዳን የማይታጠፍ ነው።
የተሰጠውን አደራ በብቃት መወጣት በአስተማማኝ ምሽግ ፊት መቆምና ለሀገርና ለሕዝብ ታማኝ በመሆኑ ኅብረት የወታደሩ ጉልበት በመሆኑ ይህንን ታላቅ እሴት በቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል።
በሳሙኤል ሞሴ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
40
3
1September 9, 2026 4.1K 1