64 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ እጅ ሰጡ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ ገደብየ አካባቢና በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 64 የፅንፈኛው ቡድን አባላት የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው እጅ መስጠታቸው ተገለፀ ።
የክፍለጦር አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሸለመው ሙለታ የፅንፈኛው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እንዲገቡ ክፍለጦሩና የመከላከያ መረጃ ባደረጉት የተቀናጀ ስራ 59 ታጣቂዎች ስናይፐር፣ ክላሽና ኋላቀር መሳርያ ከነ መሰል ተተኳሹ ይዘው መግባታቸው ገልፀዋል።
በተመሳሳይ በአደርቃይ ወረዳ 05 ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምህረት ጠይቀው ለሰራዊታችን እጃቸው የሰጡ መሆኑ በ10ኛ ዕዝ የመብረቅ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ስንታየሁ ሰይድ ተናግረዋል።
አመራሮቹ አሰከትለውም ከሰላም የሚጠቀም እንጂ የሚጎዳ ነገር እንደሌለ ገልፀው በበረሀ ያሉ ታጣቂዎች እድሉን ሊጠቀሙበት እንደሚገባና ሰራዊታችን የጠላቶቻችን ሀገር የማተራመስ ህልምና ሴራ ለማክሸፍ ከምን ጊዜው በላይ በተሟላ የዝግጁነት ደረጃ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
40
17
6
3
2September 20, 2026 3.7K 5