የሴክተር አራት አዛዥ ከኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም
በሶማሊያ የሴክተር አራት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አብዱረሀማን ራያል በሴክተር አራት ስር ሆኖ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ድጋፍና ማረጋጊያ ተልዕኮ ላይ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮች ጋር በሀልጌን ተወያዩ።
አዛዡ በዉይይታቸዉ ኢትዮጵያ በሶማሊያና በቀጣናዉ የተረጋጋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ፅኑ አቋም እንዳላትና ለዚህም አዎንታዊ ሚና እየተወጣች መሆኗን እንደሚረዱ አብራርተዋል።
በሶማሊያ ተልዕኮ ላይ የሚገኘዉ ሰላም አስከባሪ የተሰጠዉ ግዳጅ ሀገሪቱ በሂደት ራሷን ችላ የፀጥታ ስራዎችን እንድትሰራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሆነ ያነሱት አዛዡ በዚህ ሂደት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በሀልጌን አካባቢ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ላይ ያለዉ ሻለቃ አመርቂ የግዳጅ አፈፃፀም ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
በሴክተር አራት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አዛዥ ኮሎኔል ወንድሙ ነሞምሳ በበኩላቸዉ የሀልጌን አካባቢ ከአልሸባብ ስጋት እንዲላቀቅ የሰላም አስከባሪ ሻለቃዉ አመራርና አባላት ተልዕኳቸዉን በጀግንነትና በዲሲፕሊን ሌት ከቀን እየተወጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠርና የመረጃ ምንጭ በማድረግ የአካባቢዉን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ግዳጃቸዉን ዉጤታማ አድርገዉ እየፈፀሙ እንደሚገኙ የገለፁት ደግሞ የሻለቃዋ አዛዥ ኮሎኔል አዱኛ ማሞ ናቸዉ። የዘገበው ታገል አልማዉ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
17
8
7
2September 20, 2026 2.9K 2