በ10ኛ ዕዝ ቀጠና የሠላም አማራጩን የተቀበሉ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ ሰጡ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

በ10ኛ ዕዝ ቀጠና የሠላም አማራጩን የተቀበሉ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙርያ ወረዳ ሰራ፣ መረባና በለሳ ዙርያ እንዲሁም በአዲ አርቃይ ወረዳ አርማደጋና ቤተማርያም አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሰላም አማራጭን በመቀበል ለሠራዊቱ እጅ መስጠታቸው ተገልጿል።

ከሰሞኑ በድምሩ 94 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለሠራዊታችን እጃቸው እንደሰጡ የዕዙ መረጃና የመብረቅ ክፍለጦር አመራሮች ተናግሯል።

እጃቸው የሰጡ ታጣቂዎቹም እስከአሁን ዓላማ በሌለው እና ህዝባችን በማይጠቅም ስራ ተሰማርተን አካባቢያችንን እና ህዝባችንን በድለናል፤ አሁን ግን የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ መንግስትና ህዝብን ሠላምን በማረጋገጥ እንክሳለን ብለዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤14👍14👏3👎1🔥1
September 8, 2026 2K 2