ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሠራዊት በጽናት የተሸመኑ የህብረ-ቀለማት ክሮች
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ሀገር በቀል ጋቢ ወይም ነጠላ ለመሥራት ሁለት መሠረታዊ ፈትሎች ያስፈልጋሉ። ድር፡- በቁመት የሚዘረጋው እና ማግ፡-በአግድም የሚሸመነው፡፡ በብዝሃነትና አንድነት ዘውግ ድርና ማጉ የተለያዩ ክሮች ቢሆኑም፣ በሸማኙ እጅ ተስማምተውና ተሳስረው ሲሸመኑ ግን መለያየት የማይችሉ አንድ ጠንካራ ልብስ ይሆናሉ፡፡ ኢትዮጵያዊነትም እንዲሁ ነው፡፡
የሠራዊታችን ኅብረ-ብሔራዊ ስብእናም የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና የማህበረሰብ ክሮች አንድ ላይ ተሳስረው የፈጠሩት ውብና የማይበጠስ የጋራ ማንነት ነው፡፡ ሽመና ከፍተኛ ትዕግስትን፣ ጥንቃቄንና ጥበብን ይጠይቃል፡፡ ኢትዮጵያዊነትም በዘመናት ሂደት ውስጥ በታሪክ ፈተናዎች አልፎ፣ በትውልዶች መቻቻልናኀ
ተኀተ አብሮነት የተሸመነ የጥበብ ውጤት ነው፡፡
በነጠላ ወይም በጋቢ ጫፍ ላይ የሚሠራው ውብሀኀ የጥበብ ቀለም የኢትዮጵያዊነትን ባህላዊ ውበት፣ ክብርና ታላቅነት ያሳያል፡፡
ኢትዮጵያዊነትን የእውነት የሚኖረው ሠራዊታችን በዚህ የሽመና ተምሳሌት ውስጥ የመከታ፣ የጽናትና የህብር አይበገሬነትን አጋምዶ የማጽናት ሚና አለው፡፡ የሽመና ክሮች እንዳይበታተኑና ውሉ እንዳይፈታ የሚጠብቅ መዋቅር ማስፈለጉ እሙን ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ሠራዊት የተለያየ ማንነት ያላቸውን የኢትዮጵያን ልጆች በአንድ ዓላማ ስር አሰልፎ፣ የሀገርን ሉዓላዊነትና አንድነት የተሸመነውን ጨርቅ ሳይቀደድና ከስብእናው ከፍታ ሳይወርድ ጠብቆ የሚያቆይ የጽናት ምሰሶ ነው፡፡
ሠራዊቱ በተለያዩ የጥንትና የዘመናዊ ታሪኮች በእንደነ አድዋ፣ ካራማራ፣ ባድመ እና ሌሎች ያሳየው ተጋድሎ፣ ኢትዮጵያዊነት የተባለው ልዕለ ውብ ማንነት በባዕዳን እጅ ክብሩ እንዳይረከስ ያደረገ የጽናት ማረጋገጫ ነው፡፡
በሠራዊቱ ውስጥ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ልጆች በአንድ ጥላ ስር ደማቸውንና አጥንታቸውን ገብረው ሀገርን ጠብቀው ያፀናሉ፡፡ ይህ ራሱ ድርና ማጉ ተሳስረው ጠንካራ ጋሻ የመሠረቱበት ህያው የሽመና ማሳያ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በብዙ ህብረ-ቀለማትና ክሮች የተገመደ፣ በታሪክ ማሽን ላይ የተሸመነ ውብ ልብስ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሠራዊት ደግሞ ይህ ጨርቅ እንዳይቀደድ፣ የክሮቹ ውሎች እንዳይፈቱና ውበቱ እንዳይደበዝዝ በደምና በጽናት የጠበቀና የሚጠብቅ የሀገር ዋስትና ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
9
7
1September 8, 2026 1.3K